የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት

ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተከሰሱ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችን የተከሳሽነት ቃል መቀበሉን ዛሬም ቀጥሎ ዉሏል።ቃሊት ያስቻለዉ የፍርድ ቤቱ አራተኛ መደበኛ ችሎት ትናንት የአንደኛ ተከሳሽ የአቡበከር አሕመድን ቃል አድምጦ ነበር።ዛሬ ደግሞ የሁለተኛ እና የሰወስተኛ ተከሳሾችን ቃል አድምጦ የተቀሩትን ተከሳሾች ቃል ለማድመጥ ለነገቀጠሮ ሠጥቷል።ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል አሸባሪዎች እንዳልሆኑ፤ እስር ቤት ዉስጥ እንደተደበደቡ፤ እንደተሰቃዩና ያልተናገሩትንና ያላሉትን እንዳሉ ተደርጎ እንዲፈርሙ መርማሪዎች እንዳስፈራሯቸው ገልፀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የችሎቱን የዛሬ ዉሉ ተከታትሎት ነበር።

የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ሒደት ዝርዝር ዘገባ

Leave a comment