የዝቋላ ገዳም ጉዳይ እያወዛገበ ነው (ደብዳቤዎቹን ያንብቡ)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በቢሾፍቱ ከተማ (ደብረዘይት) በሚገኘው የዝቋላ ተራራ ላይ፤ ከዚያም በሚገኘው የጸበል ስፍራ በመጪው መጋቢት ወር የ እሬቻ በአል እንደሚከበር፤ በተለይ በሬድዮ እና በቴሌቭዥን ከተነገረ በኋላ ሁኔታው ውጥረትን ፈጥሯል። ከዚህ በፊትም ቢሆን፤ የቀድሞው ፓትርያርክ በነበሩበት ወቅት ይኸው ጉዳይ አወዛጋቢ ሆኖ እንደነበር እና ለግዜው ግን ሁኔታዎችን ለማርገች ሲሞከር መቆየቱ ይታወሳል። የዚህ አመቱ አከባበር ግን በተለይ በሚድያ መሰራጨቱ ውጥረቱ እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል።

በዚህም መሰረት የገዳሙ አባቶች ለአቡነ ማትያስ የጻፉትን ደብዳቤ ተከትሎ፤ ፓትርያርኩ ደግሞ ለኦሮምያ ፕሬዘዳንት እና በግልባጭ ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት የጻፉትን ደብዳቤ ከዚህ በመቀጠል አቅርበናል። ደብዳቤዎቹ በራሳቸው የሚነግሩን ፍሬ ነገር በመኖሩ፤ በጽሞና እንዲያነቡ ጋብዘናል።

Zequala

zeQuala1

 

ethioforum.org

Posted By/ Lemlem Kebede

Advertisements