ስንት ትውልድ እስኪጠፋ እንጠብቅ? (ፍርዱ ዘገዬ)

ECADF Ethiopian News and Views in Amharic

ጠባብነትና የግንዛቤ ዕጥረት ደግሞ ጓደኛሞች ናቸው፤ ብዙ ነገርም ያሳጡሃል – ለምሣሌ ማኅበራዊ እንስሳነትህን በማስረሳት የሁሉምነትህን ትተህ የጥቂቶች ወገን ብቻ እንድትሆንና ለጥቂቶች ልብህን ለብዙዎች ግን ጥርስህን እንድትሰጥ ያስገድዱሃል፤ ሃይማኖትህን ያስክዱህና በዘረኝነት ልምሻ ኮድኩደው በከረፋ መሬት ላይ የዘውግ አባላትህን ትፈልግ ዘንድ የእንፉቅቅ ያስኬዱሃል፤ ከሌላ ዘውግ ጓደኛና ወዳጅ ቢኖርህ እሱንም ያስክዱህና በጠባቧ የዘውግ ክፍልህ አውርደው የገማ የገለማ የአጥንትና ደም ጭቃ ውስጥ እንድትንቦራጨቅ ያደርጉሃል፡፡

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements