አቡጊዳ – ሐዋሳ በዘር/ቋንቋ ግጭት ቀዉስ ዉስጥ ናት

awassa1.jpg

«በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውም ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ፣ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል» ሲል ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ ዘገበ።

በአዋሳ የታቦር 2ኛ ት/ቤት በተጨማሪ ሌላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቤት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ረብሻ ተነስቷል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት በተማሪዎችና በአስተማሪዎች ላይ መድረሱን ያከለው ጋዜጠና ዳዊት፣ «የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ቋንቋ እንዲለወጥ በጠየቁ የኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ተወላጆች መካከል ረብሻው መቀስቀሱን ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች በስልክ ገልጸውልኛል፡፡ረብሻውን ለማብረድ ፖሊሶች መሳሪያ መተኮስ በመጀመራቸውም የተጎዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡በአሁኑ ሰዓት ሐዋሳ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ያለ ማቋረጥ እንደሚሰማም ምንጮቼ ነግረውኛል፡» ሲል በአዋሳ የተፈጠረዉን አሳዛኝ ክስተት ያብራል።

ቋንቋ የመገናኛና የመግባብያ መሳሪያ እንጂ የጠብና የጦርነት መንስኤ መሆን እንደሌለበት የሚናገሩት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ በቅርቡ በባህር ዳር በኦሮምኛ ተናገሪዎችና አማርኛ ተናገሪዎች መካከል የተፍጠረው ግጭትና በአምቦ አማርኛ ተናገሪዎች «ከአገራችን ዉጡልን» ተብሎ የደረሰባቸው እንግልትንም በማስታወስ፣ ኢሕአዴግ እያራመደ ያለው የጎሳ ፖለቲካ ያመጣው መዘዝ እንደሆነ ይናገራሉ። « ዜጎች በልዩነቶቻቸው ተከባብረው ፣ የጋራ እሴቶቻቸውን በጋራ አሳድገው እንዲኖሩ የሚያደርግ ሳይሆን፣ ጠባብነትን የሚያስፋፋ» ነው ሲሉም የአዋሳዉ ብጥብጥ ኢሕአዴግ ወለድ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል።

Source/abugida ethiopian.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s