አዲስ አበባ-ኢትዮጵያዊዉ ጋዜጠኛዉ እንዲፈታ ሲፒጄ ጠየቀ

የሐሰት ዜና በመዘገብ ወንጀል ባለፈዉ ሳምንት እስራት የተበየነበት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አስፋዉ ብርሐኑ እንዲለቀቅ የጋዘጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ ሲፒጄ ጠየቀ።የቀድሞዉ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ አሰፋ ብርሐኑ የተወነጀለዉ ሥልጣናቸዉ ላይ የሚገኙ ሰወስት የመንግሥት ሹማምታት ከሥልጣን ተነሱ ብሎ በመዘገቡ ነዉ።ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባዉ ሐሰት መሆኑን አምኖ ይቀርታ ጠይቋል፥ ጋዜጠኛዉንም ከስራ አቧሮታል።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ እንደሚለዉ ጋዜጣዉ ለሥሕተቱ ይቀርታ ከጠየቀና ዘጋቢዉን ከተቀጣ ጋዜጠኛዉ ተጨማሪ ቅጣት ሊበየንበት አይገባም። ባለፈዉ ሳምንት ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ግን ጋዜጠኛ አስፋዉን በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር እስራት በይኖበታል።ኮሚቴዉ እንደሚለዉ የኢትዮጵያ በርካታ ጋዜጠኞች ከታሠሩባቸዉ ጥቂት የዓለም ሐገራት አንዷ ናት።

Source-www.dw.de.com
Posted by- Lemlem Kebede

Advertisements