461  461 ሰሜን ጎንደርን በ3 ዞን መከፋፈልና ማዳከም¡¡ ከሱዳን ደንበር ጋር ያለውን መቁረጥ¡¡¡ ጎንደርን ቅማንትና አማራ ብሎ መከፋፈል¡¡¡¡

ሙሉነህ ዮሃንስ

ነሃሴ 25 2009

ወገናችን የሆነው የቅማንት ህዝብ ብዛት ወያኔ በቆጠረው መረጃ ብንሄድ እንኳን 170 ሺህ ነው። ከዚህ ውስጥ ቋንቋውን መናገር የሚችለው ወደ 1625 ሰው ነው።


በግልባጩ የወልቃይት ሁመራ ጠገዴና ጠለምት 4 ወረዳ ህዝብ በምክንያታዊ ግምት 700ሺህ ይጠጋል። ይህም ሲሆን የሰሜን ጎንደርን ህዝብ 4 ሚሊዮን ሲያደርሰው በአጠቃላይ 7 ሚሊዮን የጎንደር ህዝብ አለ።

ታድያ ከ7 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ለ170 ሺህ እጅግ በሁለንተናው ከ98% አማራ ጋር ለተሳሰረ ቅማንት የመነጣጠል ስራ የጠላት ነው እንጅ መች የወዳጅ ነው!

በወያኔ እሳቤ ከተሄደ ወደ 5 ሚሊየን የሚጠጋው ታላቁ የሲዳሞ/ሲዳማ ክፍለሃገር ህዝብ እውቅና ይሰጠኝ ስላለ ከ20 አመት በላይ ሲጨፈጨፍ ከርሟል። ትግራይ ውስጥ ትግሬ አይደለንም ያሉ የኢሮብ ብሄር ተወላጆች አይቀጡ ቅጣት ነው ሲደርስባቸው የኖረ። አንድ ወቅትማ ፓርቲም እንደነበራቸው እናስታውሳለን።

ስሌቱን ካሰፋነው የ OPDO ባለስልጣናት ባመኑት 11ሚሊዮን አማራ በኦሮሞ ክልል ይኖራል። ያ ህዝብ ለምን ልዩ መብት አልጠየቀም ወይም አልተጠየቀለትም? በአማራው ክልል የኦሮሞ የአገውና አሁን ደግሞ የቅማንት ልዩ ዞኖች ተቋቁመዋል። ይህ አካሄድ ሌላ ሳይሆን ወያኔ አማራን አዳክሞ ኢትዮጵያን የማፈራረስ እቅዱ አካል ነው።

የጎንደር/የአማራ ህዝብ ወልቃይትንና ራያን መልሱ ብሎ ገፍቶ ሲመጣባቸው ወያኔወች በአንድነት ፀንቶ የሚኖረውን የጎንደር ህዝብ የቅማንት ጉዳይ ብለው አጀንዳ አመጡ። ይገርማቹሃል የወያኔ ካድሬወች ሳት ብሏቸውም የቅማንት ሪፈረንደም ወደ ጎንደር ወይም ወደ ትግራይ እንከለል ብሎ መምረጥ ስለመሆኑ ዳዊት ከበደ የሚባለው ጥምዝ ወያኔ ያለውን ከተያያዘው መረጃ እዩት።

ደርግ መውደቂያው ላይ ቅይጥ ኢኮኖሚ ቅብርጥሴ ሲል እናስታውሳለን። ወያኔም መቀበሪያቸው የሆነውን የወልቃይት ጥያቄ ብሎም ጎንደርን ከሱዳን ድንበር ነጥሎ ወደ ትግራይ የመውሰድ አጀንዳቸውን ለማስፈፀም የቅማንት ጥያቄ ብለው እያደናገሩ ነውና ወገን ነቅተህ አረሙን ንቀል። ቅማንት ጀግና የጎንደር ህዝብ ነው የትግሬ መርዛማ ፖለቲካ ማስፈፀሚያ አይሆንም።

 0  461  461

Advertisements