ሕወሃት የትግራይ ልዩ ሃይል አባላትን የአማራ ልዩ ሃይልን የደንብ ልብስ አልብሶ አማራውን እንዲጨፈጭፉ አሰማርቷል

በማኅበራዊ ገጾች እየተሰራጩ ያሉ ታማኝነት ያላቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት “የአማራ ልዩ ሃይል አቋም ይዟል” ተቃውሞ በማሰማት ላይ ባሉ ወገኖቹ ላይ አልተኩስም ብሏል። ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) ይህ ነገር እጅግ አስደንግጦታል።

ከውስጥ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሕወሃት በአማራው ክልል የአማራ ልዩ ሃይልን መለዮ እና የደንብ ልብስ ያጠለቁ ከትግራይ ያመጣቸውን “የትግራይ ልዩ ሃይል” አባላት ተቃውሞ በማድረግ ላይ ያለውን የአማራ ሕዝብ እንዲጨፈጭፉ እያሰማራ እንደሆነ የሚያረጋግጡ አስተማማኝ መረጃዎች ወጥተዋል።

በጎንደር የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ሴራውን ተረድተው የማግለል እና ሌሎች እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው።

ይህን መረጃ እያሰራጩ ያሉት ምንጮች እንዳሉት “ከእንግዲህ የአማራውን ልዩ ሃይል መለዮ አጥልቆ ህዝቡን የሚገድል የሚደበድብ ካለ እሱ የትግራይ ልዩ ሃይል አባል ነው። ይህ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።”

በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቀደም ብለው እንደተናገሩት ሕወሃት በጨፍጫፊነቱ የሚታወቀውን የአጋዚ ሰራዊቱን የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ አልብሶ የተቃውሞ ሰልፈኞችን ለመግደል እየተጠቀመበት መሆኑን መዘንጋት የለበትም።

እውነተኞቹ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሕወሃት ሥርዓትን በመንፈስ ተለይተውታል። አንዳንዶቹ በአካልም ሕወሃትን እየከዱ መሳሪያቸውን ለሕዝቡ አስረክበው ተሰውረዋል።

የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት አፈሙዛቸውን ወደ ዘረኛው እና አምባገነኑ የሕወሃት ሥርዓት አዙረው የሕዝብ ወገተኝነታቸውን ከዳር እስከዳር የሚያስመሰክሩበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።

 

ecadforum.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements