በባህርዳር የተዘጋጀው የነኩኩ ሰብስቤ ኮንሰርት ላይ ቦምብ ተወረወረ | ኮንሰርቱ ተቋርጦ ተኩስ እየተሰማ ነው

በደረሰው መረጃ መሠረት በባህርዳር ከተማ በትግራይ ነጻ አውጪው ሕወሓት/ የቢራ ፋብሪካ በሆነው ዳሽን ቢራ ስፖንሰርነት ዛሬ ሲደረግ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ቦምብ ተወርውሮ ኮንሰርቱ መቋረጡና ሕዝቡ መበተኑ ተሰማ::

የዘ-ሐበሻ የባህርዳር የዜና ምንጮች እንደገለጹት ሕዝቡ ዳሽን ቢራን መጠጣት የወገንን ደም መጠጣት ነው በሚል ቦይኮት ያደረገው ሲሆን በዚህም ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የወደቀው ዳሸን ቢራ “ባለአገር” የሚል ቢራ በመጀመር ሕዝቡን ሊያደናገር ቢሞክርም መረጃው ሕዝቡ ጋር ቶሎ በመድረሱ ባላገሩ ቢራም እንዲሁ በሕዝብ ማ ዕቀብ እንደተጣለበት ይታወቃል::

“ባለአገር” ቢራ ስፖንሰር ያደረገው ይኸው ኩኩ ሰብስቤ; ማህሙድ አህመድና አረጋኸኝ ወራሽ የሚሳተፉበት ኮንሰርት እንዲሰረዝ አዘጋጆቹ ቢጠየቁም እምቢ ማለታቸው ይታወሳል:: የባህርዳር ህዝብ “እኛ እየሞትን በደማችን ላይ አትጨፍሩ በሚል” ለዘፋኞቹ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር:: ማረጋገጥ ባንችልም ማህሙድ አህመድ ኮንሰርቱን ቀድሞ የሰረዘ ቢሆም ኩኩ ሰብስቤና አረጋኸኝ ወራሽ ኮንሰርቱን ሳይሰርዙ ጀምረውት ነበር::

ቀድመው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የነበርቱት የባህር ዳር ወጣቶች በዳሽን የቢራ ኮንሰርት ላይ 2 የቦምብ ጥቃት ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ ሲያደርሱ ከተወረወሩት ሁለት ቦምቦች አንደኛው ሲከሽፍ አንደኛው ያደረሰው ጉዳት አልታወቀም:: ሆኖም በአካባቢው በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ተኩስ እሩምታ የሚሰማ ሲሆን ኮንሰርቱም እንደተበተነ ለመረዳት ተችሏል::

ጉዳዩን የበለጠ አጣርተን ይዘን እንመለሳለን::

Advertisements