የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ አካባቢ ጥቃት ፈፀመ

January 31, 2014

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የአገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንባር ለሱዳን ለማስረከብ ሽር ጉድ እያለ የሚገኘውን የወያኔን አገዛዝ ጸረ-አገርና ጸረ-ህዝብ እንቅስቃሴ በመቃወም በመተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተባለ ቦታ ከወያኔው 24ኛ ክፍለ- ጦር ጋር በጥር 21- 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሠዓት ላይ ባደረገው ውጊያ 14(አስራ አራት) ገድሎ 12(አስራ ሁለት) አቁስሏል።Ethiopian freedom fighters

በመተማና አካባቢው በተደጋጋሚ በአርበኛው ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የወያኔው ቅጥረኛ ሠራዊት ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው እየፈረጠጠ መሆኑ ሲታወቅ በደረሰበትም ጉዳት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ ሰላማዊውን ነዋሪ በእናንተ ምሽግነት ነው እየተመታን ያለነው በሚል እንግልት እያደረሱበት መሆኑ ታውቋል።

በተያያዘ ዜና በጭልጋ ወረዳ ጫቁ የተባለ አካባቢ ነዋሪዎች ከብት፣በግና ፍየል በአካባቢው የወያኔ ታጣቂዎች እየታረደ እየተበላባቸው መሆኑ ታውቋል።
በዚሁ አካባቢና አጎራባች ወረዳዎች የወያኔው ተላላኪዎች ተደጋጋሚ ንብረትን የመዝረፍ ሂደት የተቆጣው ነዋሪ ለምንድን ነው ንብረታችንን የምትዘረፉት ምን አደረግናችሁ ብለው ሲጠይቁ እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ፣መንገድ መሪዎች እንዲሁም ስንቅ አቀባዮች ናችሁ የሚል ምክንያት የሰጧቸው መሆኑ ታውቋል።

ሕዝቡም እኛ የአርበኛው አባልም ደጋፊም አይደለንም ከፈለጋችሁ እነሱን ተከታትላችሁ መዋጋት ትችላላችሁ እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉ? ሲሉ ምሬታቸውን ቢገልፁም እንግልቱ እንዳላበራ ዘጋቢያችን ካደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

ዘጋቢያችን አክሎ እንደገለፀው የወያኔው ተላላኪዎች በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ያለው እንግልት ያስቆጣቸው ብዛት ያላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ሠራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን አስታውቋል።

በሌላ ዜና የአማራ ክልል ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው ሙሉጌታ ወርቁ የተባለው ግለሰብ በክልላችን ቢሮዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰዎች ተሰግስገዋል በሚል ምክንያት ሰሞኑን በየወረዳው ፅ/ቤት የማፅዳት ዘመቻ በሚል ከፍተኛ ስብሰባ እያደረገ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተደጋጋሚ ጥቃት እያሰጋው የመጣው ሆድ አደሩ የአማራው ክልል ባልስልጣናት ሕዝቡን በተለያየ ምክንያት ማሰቃየቱ ሳያንሰው የራሱ ታማኝ የሆኑ ቅጥረኞቹ ላይ እምነት በማጣት የሚያደርገውም የጠፋበት መሆኑ ግልፅ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነ የዚሁ ችግር ሰለባ ልንሆን እንችላለን ያሉ ወገኖች ጠቁመዋል።

በይበልጥ አማራዉን በማይወክሉት የወያኔ አገልጋዮች እየተሰቃየው ያለው ሕዝቡ ሲሆን ፣ እነሱም ሕዝቡ ከጎናችው አለመኖሩን በመረዳታቸው የተፈጠረው ክፍተት በፈጠረባቸው ጭንቀት የመንግስት ሠራተኛውንም ሆነ ነጋዴውን ማመሱን እንደቀጠሉበት ለማወቅ ተችሏል።

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ የነበረው የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ተገደለ

ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።

ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።

በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪውን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር

Source/www.ecardf.com

Posted by/Lemlem Kebede

Advertisements