የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት (ክፍል 6)… ዘረኝነት በህወሓት የመከላከያ

samora Yenus

ህወሓት ለዕለት ጉርሳቸው ብቻ ሲሉ የመከላከያ ሰራዊቱ አባል የሆኑ የደሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆችን በገፍ እየገበረ በእነሱ ደም እና አጥንት ነግሶ ረግጦ ሲገዛ ለመኖር በመከላከያው ውስጥ ከሚጠቀምባቸው ስልቶች ዋነኛው እና ቁልፉ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን ከታች እስከ ላይ በሚገኙ የአዛዥነትና የሓላፊነት ቦታዎች በማስቀመጥ ነው፡፡ የህዝብ ልጅ የሆነው ሰራዊት የህወሓትን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሲባል ብቻ በየበረሃው እንደቅጠል እየረገፈ የሚገኘው እና የቀረውም አስተዳደራዊ በደል እየደረሰበት መብቱን እንዳይጠይቅ ተደርጎ በመቀፍደድ መላዎሻ አጥቶ የሰቆቃ ህይወት እየገፋ የሚገኘው ከጓድ መሪ ጀምሮ እስከ ኤታማጆር ሹሙ ድረስ ለህወሓት ታማኝ በሆኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች መሪነት ተጠርንፎ በመያዙ ነው፡፡ ይህ በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የለየለትና ዓይን ያወጣ ዘረኝነት ሰራዊቱን ከገጠሙት በርካታ የወቅቱ ችግሮች ዋነኛው ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ የሚብሰው ራሱን ህወሓትን ነው፡፡ በመከላከያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ምድር አፈር ላይ የበተነው የዘረኝነት ዘር በቅሎ በማደግ በጊዜ ሂደት ጥሻ ሆኖ ህወሓትን በቁሙ ውጦ ደብዛውን እንደሚያጠፋው የተረጋገጠ ነው፡፡ ህወሓት በየጎጡ የቀበረው የመንደርተኝነት አውዳሚ ፈንጅ ከወዲሁ በአፋጣኝ ካልከሸፈ ከእሱ አልፎ ኢትዮጵያን በጣጥሶ ሊያፈርሳት እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡፡ ህወሓት የትግራይ ብሄር ተወላጅ ብቻ የሆኑ ታማኝ ሰዎቹን በመሾም በዘር የዕዝ ሰንሰለት እግር ከወርች አስሮ ለስልጣኑ አድባር መሰዋዕት ሊያቀርበው ለዕርድ ያዘጋጀው ሰራዊት የህወሓት ጀምበር ልትጠልቅ ስታዘቀዝቅ የጠብመንጃውን አፈሙዝ ወደራሱ ወደ ህወሓት አዙሮ የሚተኩስ መሆኑን ለመናገር ነብይ መሆን አያሻም፡፡ በርና መስኮቱ በተዘጋ ቤት ውስጥ በባለቤቱ የሚደበደብ ውሻ መሹለኪያ ቀዳዳ ስለሌለው ብቸኛው አማራጩ በስለታም ጥርሶቹ ደብዳቢ ባለቤቱን ዘነታትሮ መጣል ስለሆነ፡፡ ህወሓት በመከላከያ ኃይሉ ውስጥ ያሰፈነውን ገደብ የለሽ ዘረኝነት ለማረጋገጥ ዋና ዋና የሚባሉ የአዛዥነትና የአስተዳደር ቦታዎችን በዝር ዝር መመልከት ይቻላል፡፡ • የመከላከያ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ (ህወሓት) • የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀ ገ/ኪዳን ገ/ማሪያም (ህወሓት) •የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር (ህወሓት) •የመከላከያ በጀትና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ምዑዝ አብረሃ (ህወሓት) •የመከላከያ የኪነ-ጥበባት ስራዎች ኃላፊ ኮ/ል ክብሮም ገ/እግዚአብሄር(ህወሓት) •የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን መምሪያ የግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል ነጋሲ ትኩ (ህወሓት) •የመከላከያ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ገ/ትንሳይ ሀጎስ (ህወሓት) •የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ ሌ/ጀነራል ሳዕረ መኮንን (ህወሓት) •የመከላከያ ሎጀስቲክ መምሪያ ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ኢብራሂም አብዱል ጀሊድ (ህወሓት) •የመከላከያ ኢንደስትሪ ኃላፊ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኛው (ህወሓት) •የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ኮማንዳንት ብ/ጀነራል ኃለፎም እጅጉ (ህወሓት) •የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ኃላፊ ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ (ህወሓት) •የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ ብ/ጀነራል ገ/እግዚአብሄር በየነ (ህወሓት) •የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ (ህወሓት) •የብርሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ኮ/ል ጌታሁን ካህሳይ (ህወሓት) •የብላቴ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ(ህወሓት) •በልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የልዩ ኃይልና ፀረ-ሽብር ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ ሻለቃ ተክላይ ወ/ገብርኤል (ህወሓት) •የሜ/ጀነራል ሃየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ ኮ/ል ጎይቶም ፋሩስ (ህወሓት) •የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮ/ል አደም ትኩ (ህወሓት) •የሜ/ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ(ህወሓት) •የሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጅነርኢንግ ኢንደስትሪ ዋና ኃላፊ ኮ/ል ሀድጉ ገ/ጊዮርጊስ (ህወሓት) •የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነርኢንግ ኢንደስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ (ህወሓት) •የመከላከያ የኮንስትራክሽንና ኢንጅነርኢንግ ማሽነሪ ኢንደስትሪ ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ካህሳይ ክዕሽን (ህወሓት) •የመከላከያ መሰረታዊ ልማትና ግንባታ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ (ህወሓት) •የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ኢንደስትሪ ም/ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አማኑኤል አብረሃ (ህወሓት) •የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንደስትሪ ፋይናንስ ኃላፊ ሌ/ኮ ለተብርሃን ደመወዝ (ህወሓት) •የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ሓጎስ አስመላሽ (ህወሓት) •የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ፀጋዬ ግርማይ(ህወሓት) •የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግንኙነትና ስርአት ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ኮ/ል በርሄ አረጋይ(ህወሓት) •የመከላከያ ፋውንዴሽን ኃላፊ ብ/ጀነራል ያይኔ ስዩም (ህወሓት) •የሽሬ ከተማ ኮሪደር ሜንተናንስ ኃላፊ ኮ/ል አብረሃ ገ/መድህን(ህወሓት) •የብሄራዊ ተጠባባቂ ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ማሞ ግርማይ (ህወሓት) •የኢንሳ /ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ ዳይሬክተር ሜ/ጀነራል ተ/ብርሃን ካህሳይ •የኢንሳ ም/ዳይሬክተር እና የጂኦ ስፓሻል /Geo-spatial/ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ታዜር ገ/እግዚአብሄር …………………. በዕዞች፣ በክፍለ ጦሮችና በሬጅመንቶች ደረጃ እንዲሁም በአየር ኃይል ውስጥ የሚገኙትን በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዙትን የኃላፊነት ቦታዎች ደግሞ ሳምንተ በክፍል 7 በዝር ዝር እንመለስባቸዋለን፡፡

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements