“ከሚነቀለው እምቦጭ አረም በላይ የተነቀለው የመለያየት መንፈስ ሚዛኑን ደፋ

 

የደብረማርቆሱ ትዕይንት ባህርዳር ላይ ይደገማል በሚል ስጋት #የኦሮሞ_ወጣቶች_ባህርዳር_እንዳይገቡ_ተደርጓል። ሰው ሳይሰማ ማምሻውን ከጎንደር ወደባህር ዳር በማስገባት ሌሊቱን ሊወስዷቸው እንዳቀዱ ይነገራል።

የጎጃም ሰው ተቀብሎ ለአገው ምድር ሰው ፣ ባህርዳር ደርሰው “ጣናን እግዜር ይማርህ፣ ጣና ኬኛ ብለን መጠናል፤” ብለው ከእንቦጭ ጋር ሲተናነቁ የጎንደር ሰው ደግሞ “እንዴታ ሳትጠይቁን”ብሎ ወደ ፋሲል ከተማ ወገን ጥየቃ ጎራ ብለዋል፡፡

ማታ ባህርዳሬ እያሉ በሃገርኛ ዜማ ኦሮምኛውን ከአማርኛው እየቀላቀሉ ጣዕም ፈጥረው በባህርዳር ከትመው ያድራሉ፡፡

ሆቴሎቹ ቄጠማ ጎዝጉዘው ቤት ለእንግዳ ከማለት ባለፈ ለኮሚቴው እንግዳ መቀበያ ለዚህ ያልሆነ ብለው ገንዘብ እያወጡ ነው፡፡

#ኦሮማራ ኦቦሉማ
ጎንደር ትልቅ የአገር ድምፅ ፣ የአገር ዋልታ ፣ የአንድነት መሰረት ፣ የማዕከላዊ መንግስት ፈር ቀዳጅ ወጣኝ ፣የስለጡን ህዝብ መናገሻ ….ጎንደር ብዙዋ ፣ ጎንደር ….”የኦሮሞ ወጣቶች ግድያ ይቁም!!” ባለች በአመቱ የኦሮሞ ወንድሞች ሊጎበኟት ቅርሷን ሊያደንቁ ፣ የወንድማማችነትን ቃልኪዳን ሊያጠብቁ ይሔው ስለ እውነት በገሃድ የኢትዮጵያዊነትን ቅኔን ተጀቡነው ከጀግኖች ከአባጃሌው ከተማ ገብተዋል፡፡

የዘመኔ ገረሱ ዱኪ ፣ የዘመኔ ጃጋማ ኬሎ የበረሃው መብረቆች ፣ የዚህ ዘመን ባልቻ አባነፍሶ …ዎች ሁለት ሙሉ ቢጫማ አውቶብስ ፍቅርን ከወንድምነት ግማድ ማተብ ጋር ይዘው ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ጃባዳ አማራ ፣ ጣና ኬኛ ፣ ኢትዮጵያ ቶኮማ እያሉ እየዜሙ ነው፡፡ ካላመናችሁ ስሟቸው፡፡ ይሔው፡፡

የኢትዮጵያ ሰማይ ዛሬ የፍስሃ ፀሃይን አብርታለች፡፡
የዘመኔ በላይ ዘለቀዎች ንጉሱን ከስደት የያኔው ደጃዝማች በላይ በተቀበለበት አደባባይ ፣ ለፀረ- እንቦጭ ዘመቻ የመጣውን የዛሬው ባልቻ በአገረኛ ወግ ተቀብሎታል፡፡ የአገው ምድር ደግ ሰው እግር አጥቦ አጓዛ አንጥፎ አሳድሯቸዋል፡፡

ከባርዳር ሰማይ ግርጌ አረም ተነቅሎ እየተጣለ ነው፡፡ የመለያየት አረም ፣ የመከፋፈል አረም ፣ የሴራ አረም ፣ የመርዘኞች አረም፡፡ ጣናን የወረረው እከክ በኦሮማራ ፍቅር ተነቅሏል፡፡ አረሙ እምቦጭ ብቻ አይደለም፡፡
25 ዓመት ሙሉ የገነገነውና ሃውልት ያቆሙለት አረም ጭምር እንጅ፡፡ ከቀናት ሁሉ ቀን ምንኛ የተቀደሰች ቀን አለች!!?

የጣና ህመሙ ካስቆጨን ይልቅ ያፀናልን ፍቅር በለጠ፡፡ በለጠ፡፡ በለጠ፡፡ በለጠ፡፡
ክፉ በጎውን ለየንበት፡፡
ጣና ጣና ጣና ዳጋ እስጢፋኖስ #አንድነት ገዳም…. በቢጫው ባስ ጣና ዳጋ እስጢፋኖስ አንድነት ገዳም መንነውልናል የኛ ባልቻ አባነፍሶዎች፡፡

” ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ””
ለጋራ ጠላት መቆም ከድሮ የመጣ ባህሏ ነው አገሬ፡፡ ገበየሁ ሲረታ ባልቻ የደረሰለት ‘ለት፡፡

ኦሮማራ በአንድነት የጣናን ጠላት ነቀለው፡፡ ነቀለው፡፡ ነቀለው፡፡ ነ…ቀለው!!!
ቶኪቹማ ኢትዮጵያ
ባዬ ግልቶማ ኦሮሞ
ቢያ ኬኛ ኢትዮጵያ
#Aschalew

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s