ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተመድ አስታወቀ

ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ የሀገራቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን አሁን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ እና በሌለቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ መፍትኤ ካልተሰጠው የሚያስከትለው ጠንቅ ከፍተኛ መሆኑንም ተመድ አስገንዝቧል፡፡


በተለይ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያተኮረው የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት፣ ቀጠናው ከድርቅ በተጨማሪ በእርስ በእርስ ጦርነት ጭምር እየተፈተነ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡ በተለይ ደቡብ ሱዳን በአሁን ሰዓት በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ እንደምትገኝ የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ሀገሪቱን ድርቅ በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጦርነት ሰቅዘው እንደያዟትም ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ ወይም ባጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ 24 ሚሊዬን ሰዎች በድርቅ መጎዳታቸውንም ተመድ አስታውቋል፡፡ ይህ ሁሉ ህዝብም አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ድርጅቱ በሪፖርቱ አሳስቧል፡፡ ድርቁ ወይም የረሃብ አደጋው የሌሎች ረድኤት ተቋማትን እርብርብ የሚጠይቅ እንደሆነ የጠቀሰው ተመድ፣ ለተረጂዎችም በአስቸኳይ መድረስ እንደሚያስፈልግ አሳውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ 8 ነጥብ 5 ሚሊዬን ሰዎችን እያጠቃ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ድርቁ አድማሱን እያሰፋ በመጣበት በዚህ ወቅት ለተረጂዎች እየተደረገ ያለው እርዳታ በቂ አለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለው ድርቅ ከግጭቱ ጋር ተደማምሮ ወደ አስከፊ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ የድንበር ቦታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭት፣ ለድርቅ ተጎጂዎች እርዳታ ለማቅረብ ጋሬጣ እየሆነ መምጣቱ ከዚህ በፊት ሲገለጽ ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s