አስደንጋጭ አደጋ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደረሰ | አንዲት ሴት ሕይወቷ አለፈ | አስራ አራቱ ሆስፒታል ገቡ

ከሙሉነህ ዮሐንስ

በመገንባት ላይ ያለ የጎንደር ዮኒቨርስቲ/ማራኪ ካምፓስ ህንፃ ተደርምሶ እጅግ በጣም ብዙ ሠራተኞች በዛሬው ማክሰኛ እለት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ለመወጣጫ የተገጣጠሙት የእንጨት ርብርብ በመደርመሳቸው በስራ ላይ ያሉ ወገኖች ከ6 እስከ 9 ፎቅ ከሚደርሰው ህንፃ ላይ ለመውደቅ ተዳርገዋል። ብዙወች ለሞትና ለከባድ ጉዳት መዳረጋቸው ከቦታው ተነግሮናል። የጉዳቱ ሰለባወች ብዙወቹ የቀን ሰራተኞች ናቸው። ቸቸላ ሆስፒታል በህዝብ ተጨናንቋል። ጥበቃዎች አናስገባም ብለዋል፡፡

የህንፃ ተቋራጩ አፍሮ ጽዬን ኮንስትራክሽን ሲሆን ባለቤቱም ሲሳይ የሚባል የትግራይ ባለሃብት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጎንደር ያሉ የንግድና የመንገድ እንዲሁም የህንፃ ስራወች ለትግራይ ተወላጆች ልዩ ቅድሚያ እንደሚሰጥባቸው ከአሁን በፊትም ከነማስረጃው ዘግበንባቸዋል።በህዝባችን ላይ ስለደረሰው ጉዳት በጣም እያዘንን ለተጎዱት አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኙ ወገንተኝነቱ የተሰማቸው የህክምና ባለሞያወችን ትጋት ይሻል።

በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው እንደዘገበው ጉዳቱ የደረሰው ሕንፃው ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ እንደሆነ አረጋግጠናል፤ በጠቅላላው የተጎዱት 15 ሰዎች ሲሆኑ የአንደኛዋ ሴት ሕይወት ወዲያውኑ ነው ያለፈው፡ ፡ 14ቱ ጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ በቦታው የነበሩ ሰዎች እንደነገሩን ከሆነ የደረሰው አደጋ እጅግ ሰቅጣጭ እንደሆነና ከተጎጂዎች መካከል እጃቸውና እግራቸው የተቆሩ ሰዎችም አሉበት፡፡

ግንባታውን የሚያካሒደው ዛምራ ኮንስትራክሽን የተባለ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ሲሆን ከዩንቨርሲቲው አመራሮ ጋር ባለው የጠበቀ የሙስና ሰንሰለት የተነሳ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ በመሆኑ ለንጹሓን ሰዎች መጎዳትና መሞት ምክንያት ሆኗል፡፡

ከፍተኛ ፎቆች ሲሠሩ የእንጨት መረባረብ መጠቀም እንደማይቻል አዋጅ ቢወጣም በዐማራው አካባቢ የሚገነቡ ዩንቨርሲቲዎች በሙሉ በዚህ መልኩ ነው የሚገነቡት፡፡ ከዓመታት በፊትም አፍሮ ጺዮን የተባለው ሌላው የሕወሓቶች ንብረት ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቢሮን ሲገነባ ከ30 በላይ ሰዎችን በተመሣሣይ አደጋ ጨርሷል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s