የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የፕሮቶኮል ኃላፊ በጸጥታ ኃይሉ መካከል መከፋፈል እንደተፈጠረ ተናገሩ

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የፕሮቶኮል ኃላፊ የነበሩት ሰው መንግስትን በመክዳት አሜሪካ መቅረታቸውን ገለጹ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ፕሮቶኮል ኃላፊ የነበሩት አቶ ባዬ ታደሰ ተፈሪ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት ለደህንነታቸው አስጊ በመሆኑ፣ ለስራ ጉዳይ በተላኩባት አሜሪካ ሀገር ለመቅረት ወስነዋል፡፡ አቶ ባዬ ታደሰ ወደ አሜሪካ የሔዱት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ሲሆን፣ ጉዟቸውም በ72ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ለመገኘት ነበር፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል፡፡

አቶ ባዬ ታደሰ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት እንደተናገሩት፣ በአሁን ሰዓት በስርዓቱ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ መከፋፈል ተፈጥሯል፡፡ መከፋፈሉ የተፈጠረው በመንግስት ባለስልጣናት መካከል ብቻ ሳይሆን በጸጥታ ኃይሉ መካከል ጭምር እንደሆነም አክለው ተናግረዋል፡፡ አቶ ባዬ ታደሰ በኢትዮጵያ ስላለው ስርዓት ማውራታቸውን ቀጥለው፣ በአማራ ክልል ስለተፈጠረው አመጽም ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት እየመጡ ‹‹እናንተ እዚህ ቁጭ ብላችሁ እኛ እዛ (አማራ ክልል) ጦርነት እናካሂዳለን፡፡›› በማለት ይዝቱባቸው እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ አካባቢ ስላለው ሁኔታ ገለጻ ያደረጉት አቶ ባዬ ታደሰ፣ አንዳንድ የመንግስት ሹማምንት በኃይል ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ካልገባን ብለው ግብግብ እንደሚፈጥሩም ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን ግብግብ ፈጣሪዎቹን በስም ጠቅሰው አይናገሩ እንጂ፣ ምንጮች እንደሚገልጹት ግን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ካልገባን ብለው ለጠብ የሚጋበዙት የህወሓት ደህንነት እና ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ይህን ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን እንዳልተናገሩ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ባዬ፣ ‹‹ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳውቅና፣ እሳቸው ለምን እኔ ቢሮ የደህንነት ኃላፊዎች ይገባሉ ብለው ጥያቄ ቢያቀርቡ፣ እሳቸውንም አኔንም አይምሩንም ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ይህ አባባላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ምን ያህል በህወሓት ተፅዕኖ ስር እንዳሉ እንደሚያመላክት ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የቀድሞ የፕሮቶኮል ኃላፊ አቶ ባዬ ታደሰ ተፈሪን ንግግር ያዳመጡ ታዛቢዎች፣ በኢትዮጵያ ያለው ስርዓት አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡ የሀገሪቱን የጸጥታ ኃይል የያዙት የህወሓት ደህንነቶች እንደመሆናቸው፣ በውስጣቸው መከፋፈል መፈጠሩ፣ ከዚህ ቀደም ህወሓት ለሁለት መሰንጠቁ ሲነገር የነበረውን መረጃ እውነት እንደሚያደርገው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ መከፋፈሉ የተፈጠረው በጸጥታ ኃይሉ መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በሹማምንቱ መካከል ጭምር መሆኑ ደግሞ ስርዓቱ ወደ አደገኛ ውድቀት እያመራ እንደሆነ ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡ መንግስትን ከድተው አሜሪካ ሀገር የቀሩት የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የፕሮቶኮል ኃላፊ አቶ ባዬ ታደሰ፣ ለአሜሪካ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s