ወይዘሮ አዜብ መስፍን በድጋሚ ሙልጭ ያልኩ ደሃ ነኝ አሉ September 21, 2017 | Filed under: News

BBN) የቀድሞ የህወሓት መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ምንም የሌላቸው ደሃ መሆናቸውን በድጋሚ ተናገሩ፡፡ በሀገር ውስጥ ከሚገኝ አንድ የሬድዮ ጣብያ ጋር ቃለ መልስል ያደረጉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ ስማቸው ከሙስና ጋር ተያይዞ መነሳቱም አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮዋ፣ ይህ ጉዳይ ጋዜጠኞች ያናፈሱባቸው ወሬ እንጂ ትክክለኛ ነገር እንዳልሆነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮዋ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ደሃ በመሆናቸው ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት የእሳቸውን እና የባለቤታቸውን ደሞዝ አጠራቅመው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

‹‹በሙስና የሚጠረጠር ሀብት ካለኝ ምድረ ጋዜጠኛ ያጋልጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ይውረሰው፡፡›› በማለት የተናገሩት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ እንዲህ ዓይነቱ ወሬ የሚናፈስባቸው ለምን እንደሆነ ግራ እንደሚያጋባቸውም አክለው ገልጸዋል፡፡ ወይዘሮ አዜብ ባለቤታቸው ከማለፋቸው አስቀድሞ በሰጡት አንድ ቃለ ምልልስ ላይ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት እሳቸው እና ባለቤታቸው የሚያገኙትን የመንግስት ደሞዝ እያጠራቀሙ እንደሆነ ተናግረው ነበር፡፡ ሆኖም ከወይዘሮ አዜብ ሶስት ልጆች ሁለቱ ማለትም ሰምሃል መለስ ዜናዊ እና ሰናይ መለስ ዜናዊ በአሜሪካ እና በእንግሊዝ በሚገኙ ውድ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩ ናቸው፡፡
ባለቤታቸው በስልጣን ላይ በነበሩበት በአንድ ወቅት፣ ቀዳማይ አመቤት የነበሩት ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ በአንድ ወቅት ለተወሰኑ የአፍሪካ ቀዳማይ እመቤቶች በነፍስ ወከፍ እስከ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ ገዝተው በስጦታ መልክ ሰጥተው ነበር፡፡ የህወሓት ንብረት የሆነውን ኤፈርት እያስተዳደሩ የሚገኙት ወይዘሮ አዜብ፣ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠጉራቸው ድረስ በሙስና የተጨማለቁ ስለመሆናቸው ከበቂ መረጃ ጋር ሲነገር ቆይቷል፡፡ ሆኖም ከህወሓት የበላይነት አንጻር እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ባለስልጣናትን ደፍሮ በሙስና የጠየቃቸው አካል የለም፡፡

6  1337  1345

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s