የቀድሞዋ የጉምሩክ ምክትል ዳይሬክተር ዓለምፀሐይ ግርማይ ከአገር ሊወጡ ሲሉ ተያዙ

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመንግሥት የተሰጡ መብቶች ማስፈጸሚያ ንዑስ የሥራ ሒደት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ከአገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ ዘገበ:: ሙሉ ዘገባው እንደወረደ ይኸው:-

የቀድሞዋ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ግርማይ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በመንግሥት ላይ ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ተጠርጥረው መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዋ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ ለተለያዩ ድርጅቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ከተፈቀዳላቸው በላይ እንዲያስገቡ መፍቀዳቸውን፣ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡

ከተፈቀደው በላይ ከገቢ ዕቃዎች መንግሥት ከቀረጥ ገቢ ማግኘት ይገባው የነበረውን 9,099,328 ብር እንዲያወጣ ማድረጋቸውንም ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ግለሰቧ በተጠረጠሩበት ጉዳይ ፖሊስ በማጣራት ላይ እያለ፣ ከአገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም አስረድቷል፡፡

መርማሪ ፖሊስ የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መሰብሰቡንና ለኦዲት ማቅረቡን፣ የኦዲተሮችን የምስክርነት በቃል መቀበሉንም አስረድቷል፡፡ የተጠርጣሪዋን ቃል መቀበል፣ የምስክሮችን ቃል መቀበልና ሌሎች ሥራዎችን በማከናወን ለዓቃቤ ሕግ ማስረከብ እንደሚቀረው በመግለጽ፣ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቆ ፍርድ ቤት ፈቅዶለታል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s