በጥቂት የህወሃት ጋንግስተሮች የሚመራው ፓርላማ ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያው አስቸኳይ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱን በሙሉ ድምጽ ወስኗል

የኢትዮጵያ ሕዝብ አዋጁን ጥሶት ከወጣ ግን ሰንብቷል።
በህዝብ ዘንድ “የአፈና” የተባለው ይህ አዋጅ መነሳቱ ሃገሪቱ አሁን ላለችበት ችግር መፍትሄ አይሆንም። ከአዋጁ በፊትም አፈናው ነበር አሁንም ይቀጥላል። መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው የሕዝብ ጥያቄ በአግባቡ ሲመለስ እና ይህ ለሩብ ምዕተ-አመታት በሕዝብ ላይ በመሳርያ ሃይል ተቀምጦ ያለ ሙሰኛ ስርዓት ሲቀየር ብቻ ነው።
አዋጁ የውጭ ቱሪስቶች ወደ ሃገር ቤት እንዳይገቡ እና ዲፕሎማቶች ላይ ከነበረ የጉዞ እክል በስተቀር በሕዝቡ ላይ ምንም ለውጥ አላመጣም – መኖሩ ፋይዳም አለነበረውም። አዋጁ ላለፉት አስር ወራት በመላ ሃገሪቱ ይታወጅ እንጂ ሕዝቡ ግን ተቀብሎ ተግባራዊ እንዳላደረገው እየተከሰቱ ያሉት አድማዎች እና ሕዝባዊ አመጾች ይመሰክራሉ።
የኮማንድ ፖስቱን እየመራሁ ነው የሚሉት ኦቦ ሲራጅ ፈርጌሳ “ሃገሪቱ ተረጋግታለች” ብለዋል። ይህ አባባል የኢራቁ ኬሚካል አሊን ንግግር ያስታውሰናል። ሃገር በግብር እሰጥ እገባ እና በሙስና እየተተራመሰች- የዜጎች ጥያቄ ገና ምላሽ ሳያገኝ  – መረጋጋት አለ ማለት ራስን ማሞኘት ይሆናል።
እሳቱን አዳፈኑት እንጂ አላጠፉትም። መብት እና ነጻነት የጠማው ሕዝብ ለጥይትም እንደማይመለስ ሕወሃቶች ገና አልተረዱትም።
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s