በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች የነጋዴዎች አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል

ለሳምንታት የዘለቀው የነጋዴዎች አድማ ዛሬ ሰኞ፣ ሃምሌ 17 ቀን 2009 ዓም ተጠናክሮ ቀጥሎአል። በሳሪስ፣ ኮሌፌ አጠና በሌሎችም የአዲስ አበባ የንግድ ቦታዎች የተካሄደው አድማ በታላቁ ገበያ መርካቶም ተደግሟል።
የአገሪቱ የንግድ ማእከል በሆነው መርካቶ አድማው የተጀመረው ከጠዋቱ ሲሆን፣ በርካታ መደብሮች በመሶብ ተራ፣ ሸራ ተራ ፣ ብርድ ልብስ ተራ፣ ሳህን ተራ፣ ቦንብ ተራ፣ ጎማ ተራ፣ ምናለሽ ተራና ሲዳሞ ተራ አካባቢዎች የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።
አብዱ በረንዳ፣ አዳራሽ የገባያ ማእከል፣ እድገት በአንድነት ህንጻ፣ ሚሊተሪ ተራ፣ አስፋወሰን ሆቴል አካባቢ፣ አመዴ ገበያ ማእከል አካባቢ፣ የደንብ አስከባሪዎች፣ ፖሊሶችና ከንግድና ኢንዱስትሪ የመጡ ባለስልጣናት መጠነኛ ቁጥር ያላቸው ሱቆች እንዲከፍቱ ቢያስገድዱም አብዛኞቹ ነጋዴዎች በንግድ መደብሮቻቸው አካባቢ ስላልነበሩ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። አዲስ የገበያ ማእከልና ይርጋ ሃይሌ የገበያ ማእከል አብዛኞቹ ከባለስልጣናት ጋር ግንኙነት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች የሚሸጡባቸው ስለሆኑ የነጋዴውን ጥሪ ባለመቀበል ድርጅቶቻቸውን ከፍተው ታይተዋል። በርካታ ፖሊሶችና ደህንነቶች በመርካቶ ተሰማርተዋል።
በአማራ ክልል ከተሞች አዲሱ የእለታዊ ግብር ይፋ ከሆነ በሁዋላ የመጀመሪያውን አድማ የለኮሰችው የምስራቅ ጎጃሟ የድ ውሃ ከተማ እስከ እሁድ ድረስ በተጠናከረና በተሳካ ሁኔታ አድማውን ያከናወነች ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ ሞጣ እና ቢቸና አድማውን በመጀመር ሌሎች የምስራቅ ጎጃም ከተሞች ሆነዋል። በዚህ

የሞጣ ነጋዴዎች የተጣለብን የቀን ገቢ ግምት ሆን ተብሎ እኛን ለማዳከምና ህውሃትን ለማበልጸግ ነው በማለት እየተናገሩ ሲሆን፣ ድርጅቶቻቸውን በሃይል እንዲከፍቱ ለማስገደድ የሚመጡ ባለስልጣኖችን በሚደርስባቸው ጉዳት ራሳቸው ሃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል ይላሉ።
“ይህን ጨቋኝና አረመኔ መንግስት ለመገርሰስ ቆርጠናል” የሚሉት ነጋዴዎች ፣ ጥያቄያቸው እስካልተመለሰ ድረስ በአድማው እንደሚገፉበት ገልጸዋል። የቢቸና ነጋዴዎችም አድማቸውን ሲጀምሩ ለባለስልጣኖች ማስጠንቀቂያ በመስጠት ነው። “ጥያቄያችንን መልሱ፣ አለበለዚያ በጉልበት ድርጅቶቻችንን እናስከፍታለን ብላችሁ አትሞክሩ” የሚሉት ነጋዴዎች፣ አድማው ለጥያቄያቸው መልስ እስኪመጣ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ “ደም ከመፍሰሱ በፊት ስራ ብትጀምሩ ይሻላቹሃል” በማለት ለማስፈራራት ቢሞክሩም ፣ ነጋዴዎቹ “ ጀምሩትና የማን ደም እንደሚፈስ እናያላን” በማለት መልስ መስጠታቸውን የነጋገርናቸው ነጋዴዎች ተናግረዋል።
በኦሮምያ በርካታ ከተሞች የተደረገው የነጋዴዎች አድማ በጅማ ከተማ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ወታደሮች ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሲያስገድዱ ውለዋል።

Source- esat

Posted By- Lemlem kebede

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s