በአወዳይ ከተማ የወያኔ ሰላይ ነው የተባለው ግለሰብ በቄሮዎች ተገደለ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ባለፈው ዓመት 6 ህጻናት ወጣቶችን ገድሏል ተብሎ የታሰረውና ሰሞኑን ከ እስር የተፈታው የሕወሓት መንግስት ሠላይ ነበር የተባለው አብዱ እድሪስ ዛሬ በአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች እርምጃ ተወስዶበት መገደሉ ተሰማ::

የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በሰበር ዜናው ላይ እንዳስታወቀው ይህ የወያኔ ሰላይ 6 ህጻናት  ወጣቶችን ቢገድልም ለይስሙላ በታሰሩ ወዲያውኑ ዓመት ሳይታሰር ተፈቷል:: ከተፈታ በኋላም የሟች ቤተሰቦችንና የአካባቢው ወጣቶችን ማስፈራራቱን መቀጠሉንም ዘግቧል:: መንግስት ይህን 6 ህጻናት ወጣቶችን በአወዳይ አደባባይ ላይ የገደለውን ግለስብ ከ እስር ሲፈታው ከነሙሉ ትጥቁ እንደነበር የዘገበው ኦኤምኤን በአወዳይ የሚገኙና የተደራጁት ቄሮዎች ዛሬ ገድለውታል::

እንደ ሚዲያው ዘገባ ቄሮዎቹ ወገኖቻቸውን የገደሉትንና ያስገደሉት ላይ ተመሳሳይ እርምጃዎች በተከታታይ ይወስዳሉ::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s