ቴድሮስ አድሃኖም ተመረጡ | “.. ቴድሮስን የመረጡት በእርሳቸውን ተጠቅመው በአፍሪካውያን ላይ የፈለጉትን ማድረግ የሚሹት መድሃኒት ሻጭ አገሮችና ኩባንያዎች ናቸው”

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ወ/ሮ ማርጋሬት ካን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለማቀፉ የጤና ተቋም (World Health Organization) ዳይሬክተር ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አደረጉ::

ይህን ስልጣን ለማግኘት ከኢትዮጵያ ፣ ከፓኪስታን እና ከእንግሊዝ የተወከሉ ተወካዮች ከፍተኛ የምረጡኝ ዘመቻ ሲያደርጉ የቆየ ሲሆን በሥስት ዙር በተደረገው የድምጽ አስጣጥ ነው ቴድሮስ አድሃኖም ማሸነፋቸው የተገለጸው::

ዓለማቀፉ የጤና ተቋም የተመሰረተው በ1948 ዓ.ም ኤፕሪል 7 ቀን ሲሆን፣ 61 አገራት በፊርማቸው ባጸደቁት ውል የተቋቋመ ሲሆን ያለፈው ዓመት በጀቱ 4 ቢሊዮን ዶላር ነበር። 8ኛው ተመራጭ ሆነው ያሸነፉት ቴድሮስ አድሃኖም ለ10 ዓመት ያህል ዳይሬክተር ሆነው የሚቆዩ ሲሆን በገዛ ፈቃዳቸውና የሚያስወርዳቸው ነገር ካልተገኘ በቀር ስልጣኑን ይዘው ይቆያሉ::

በሌላ በኩል ቴድሮስ አድሃኖም ከመመረጣቸው አስቀድሞ ከሕብር ራድዮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት የቀድሞው የኦነግ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃለፊ አክቲቭስት አሚን ጁንዲ “…ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለሕዝብ ጤና ግዴለሽ መሆኑን ስለሚያውቁ በዓለም ጤና ድርጅት ስም ስልጣን እንዲይዝ የሚፈልጉት ከጀርባቸው በአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ላይ እሱን ተጠቅመው የፈለጉትን ማድረግ የሚፈልጉ የመድሃኒት ኩባንያዎችና አገሮች ናቸው” ማለታቸው ይታወሳል::

(የአሚን ጁንዲ ቃለምልልስ በቴድሮስ አድሃኖም ላይ እዚህ ይገኛል) 

በሌላ በኩል በቴድሮስ አድሃኖም ጉዳይ አስተያየት ከሰጡ መካከል ዶ/ር ተሾመ ሞገሴ “ዶ/ር ቴዎድሮስ ማሸነፉ በሄደበት ሁሉ ተቃውሞ ስለሚደርስበት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የተቀመጡት የምዕራባውያን ታላላቅ ሚድያዎች ወደው ሳይሆን በግዳቸው በየለቱ የኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ ይዘግባሉ:: በማሸነፉም በመሸነፉም የሚጎዱት ህወሃታውያን ናቸው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል:

 

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s