ዶክተር ደብረጽዮን ካለመንግስት ይሁንታ ቴዲ አፍሮን ቃለምልልስ እንዲደረግ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች እንዲቀጡ አዘዙ

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ካለመንግስት ኃላፊዎች እውቅና እና ይሁንታ ከቴዲ አፍሮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ የኢቢሲ ሠራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ አስተላለፉ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ትናንት ሕወሓቱ ዶክተር ደብረጽዮን የኢቢሲን አስተዳደሮች በቴዲ አፍሮ ቃለምልልስ ዙሪያ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን አርቲስቱን ቃለምልልስ እንዲደረግ ማን እንደፈቀደ እንዲመረመር አዘዋል:: ካለባለስልጣናት ይሁንታ ቃለምልልሱ መደረጉና ቃለምልልሱ ሳይተላለፍ በፊት ማስታወቂያ መለጠፉና በኋላም አለመተላለፉ መንግስትን አሳጥቶታል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን ቴዲ ቃለምልልስ ባይደረግ ኖሮ ይህ ሁሉ ውዥንበር አይፈጠርም ነበር ሲሉ በቁጣ መናገራቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ደብረጽዮን ትናንት የኢቢሲን ማኔጅመንት የሰበሰቡት የመዝናኛ ክፍሉ ኃላፊ; ማስታወቂያውን በፌሰቡክና ዩቱብ በለቀቀው ሠራተኛና በጋዘጠኛ ብሩክ ላይ ቅጣት እንዲፈጸም ለማወጅ የነበረ ሲሆን ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ቀድሞ የሥራ መልቀቂያ በማስገባቱ ዶክተር ደብረጽዮን ምስጢር የሚያሾልክ አለ ማለት ነው በሚል በማኔጅመንቱ ላይ መጮሃቸውን ምንጮች አስታውቀዋል::

Posted By- Lemlem kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s