የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) እና የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፊርማው በኋላ ያወጡትን የጋራ መግለጫ ይዘናል

የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኦብነግ ተወካዮች ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓም በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ተገኛኝተዋል። የሁለቱ ድርጅቶች ተወካዮች የኢትዮጵያን የወቅትቱ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት መርምረዋል፤ የህወሓት/ኢሕአዴግ አምባገነን አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሰቆቃ አጤነዋል።

በአሁኑ ሰዓት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የፈጠረው ቀውስ ከኢትዮጵያ አልፎ ወደ ከፋ አካባቢያዊ ቀውስነት ሊያድግ እንደሚችል የሁለቱም ድርጅቶች ተወካዮች አጢነዋል። ይህ ሁኔታ አስጊ ሁኔታ በፍጥነት ካልተቀለበሰ ከፍተኛ ሰብዓዊና ፓለቲካዊ ቀውስ በኢትዮጵያና አካባቢዋ እንደሚመጣ የሁለቱም ድርጅቶች ተወካዮች የጋራ ስጋት ሆኗል።

የሁለቱ ድርጅቶች ተወካዮች በአገራችንና በአካባቢው ሁኔታዎች ላይ ጥልቅ ውይይት ከደረጉ በኋላ በመፍትሔ ሀሳቦች ላይ መክረዋል። የህወሓት/ኢሕአዴግ አገዛዝና የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃና ስቃይ እንዲያበቃ በጋራ ለመታገል፤ ሌሎች የዲሞክራሲ ኃይሎችን በማሳተፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ኃይል እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ለመታገል ቃል ገብተዋል።

በዚህም መሠረት ተመጣጣኝ ውክልና ወደአለበት ሀቀኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚረዱ መሠረቶች አኑረዋል። ሁለቱም ድርጅቶች በአገራችን ኢትዮጵያ ስልጣን የያዘውን አምባገን አገዛዝን በጽኑ አውግዘዋል።

ህወሓት/ኢህአዴግ ተወግዶ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ የሽግግር ሥርዓት እንዲፈጠር የሚፈልጉ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ ወደ አንድ የጋራ መድረክ እንዲመጡ ለማመቻቸት በጋራ እንደሚሰሩና ለሁለቱም ዴሞክራሲያዊ ሃይሎችም ጥሪ አድረገዋል።

የዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲቆም፤ ለዘመናት የተጫነበት አምባገነን አገዛዝ እንዲያበቃ የሚያደርገውን ትግል እንዲደግፍ ጥሪ አድርገዋል።
በመጨረሻም፣ የኢትዮጵያ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላይ እንዲሁም የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ባልደረቦች ከህገወጡ የህወአት አምባገነናዊ ሥርዓት ጎን ቆማችሁ የራሳችሁን ሕዝብ ከመፍጀትና

ከማሰቃየት ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ፤ ይልቁንም ከሕዝብ ጎን ቆማችሁ ለሁላችንም መልካም የሆነ ለውጥ ለማምጣት እንድትታገሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓም

ፍራንክፈርት፣ ጀርመን

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s