የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም የሚያስከብር አዋጅ ጸደቀ

ከሁለት ዓመት በፊት በጭምጭምታ ደረጃ ወሬዉ ወደ አደባባይ የወጣዉ ባለሥልጣናት “ጡረታ” ሲወጡ የሚከበርላቸዉ ጥቅማጥቅም አሁን “ህጋዊ  ዕዉቅና” አግኝቷል።

ሐሙስ ዕለት በዋለዉ የኢህአዴግ “ፓርላማ” የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸዉ ሲነሱ ጥቅማጥቅማቸዉን የሚያስከብር አዋጅ ተሸሽሎ እንዲጸድቅ ተደርጓል።

የተሻሻለዉ አዋጅ ከኃላፊነታቸዉ የሚነሱ የመንግስት ባለሥልጣናት እንደ የኃላፊነት ደረጃቸዉ የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣መኖሪያ ቤት፣የቤት ሰራተኞች፣ የምግብ አብሳዮች፣ የቀንና የማታ ቤት ጠባቂዎች፣ የተሸከርካሪ አገልግሎት ከነአሽከርካሪዉና ጠባቂ (body guard) እንዲሟላላቸዉ አዋጁ ያብራራል።

ቀደም ሲል ለኢህአዴግ ነባር ታጋይ ባለሥልጣናት መኖሪያ ቤት በሚል ከመንግስት ካዝና ያለ ፓርላማዉ ይሁንታ (ምንም እንኳን ልዩነት ባይኖረዉም) በአዲስ አበባ ወረገኑ አካባቢ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል “ጡረታ ለሚወጡ ስድስት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመቶ ሃምሳ አራት ሚሊዮን ብር (እያንዳንዳቸው ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ በድምሩ 154 ሚሊዮን ብር) መጦሪያ ቤቶች ተገንብተው እየተጠናቀቁ” መሆናቸውን ጉዳዩን በኃላፊነት የሚመራው ተክለጻዲቅ ተክለአረጋይ (አቡነአረጋይ) ታህሳስ 1፤2008ዓም/November 12, 2015 ለሸገር ሬድዮ መናገሩ በዕለቱ ተዘግቦ ነበር። ተክለጻዲቅ ሲቀጥልም “አገራችን እነዚህን ቤቶች ለባለስልጣኖች መገንባቷ ከአፍሪካ አንደኛ ያደርጋታል” ከማለቱ በተጨማሪ “የመዋኛ ገንዳ (ስዊሚንግ ፑል) ያላቸው እነዚህ ቅንጡ ቤቶች የሚገነባላቸው ባለስልጣኖች ተለይተው መታወቃቸውን” ማስረዳቱ የህወሃት/ኢህአዴግን ዓይነደረቅነት ያሳየ ተግባር ሆኖ ነበር።

ዜናውን አያይዞ “ከጠቅላላ ሕዝቧ ውስጥ ከ2 ፐርሰንት በታች ለሆኑ አዛውንት ዜጎቿ የጡረታና የማህበራዊ ዋስትና የሌላት አገር ብትሆንም በስልጣን ዘመናቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለዘረፉ ሌባ ባለስልጣኖቿ ግን ቅንጡ መጦሪያ ቤት የምትገነባ አገር ሆናለች” በማለት በወቅቱ በተጨማሪ መዘገቡ የሚታወስ ነው

ሳራ አሊሲዮ ከ 1ወር ህጻን ልጇ ጋር በዋርዴር – Associated Press

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የዕለት ምግብ ደራሽ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር  ህወሃት/ኢህአዴግ ባመነዉ መረጃ መሰረት 6.2 ሚሊዮን ይሆናሉ። ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 24 ሚሊዮን ደርሷል። በከተሞች እጅግ ሥር የሰደደ ድህነት ይታያል። ከዚህም አልፎ በሀገሪቱ በተከሰተዉ ድርቅ በየዕለቱ የሚሞቱ የጋማና የቀንድ ከብቶች ቁጥር እያሻቀበ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ክፍል በችጋር እየተሰቃየ ባለበት ሁኔታ ለባለሥልጣናቱ እንዲህ ቅንጡ የሆነ ጥቅማ ጥቅም የታከለበት አዋጅ ማጽደቁ የጤና አለመሆኑ አስተያየት ተሰጥቶበታል። በአዋጁ ላይ “የተሻሻለዉ አዋጅ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ይረዳል” በሚል የሰፈረው ሃሳብ “ህወሃታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ይረዳል” ተብሎ ይነበብ ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተሳልቀዋል።

ለጎልጉል ሃሳባቸውን የሰጡ የህግ ባለሙያ እንዳሉት “ዓይን ቀቅለዉ የሚበሉት የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የጡረታ ጊዜያቸዉን በቅንጡ ህይወት ለማጀብ አዋጅ እስከማሻሻል ደርሰዋል። በሥልጣን ላይ እያሉ የሚዘርፉትን ገንዘብ የት እንደሚያደርሱት አደባባይ ላይ የተሰጣ እዉነት ቢሆንም አንድ ቀን ወደ ህዝብ እንደሚመለስ ተስፋ እንደርጋለን። እስከዚያዉ ኢትዮጵያና አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የሰቀቀን ህይወት እየኖሩ በሚገብሩት ግብርና በኢትዮጵያ ሥም በሚለመነዉ ገንዘብ ዘመን ያገነናቸዉን ጅቦች ሲቀልብ ይኖራል” ብለዋል!!

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ከሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ ከጡረታ፣ ከመኖሪያ ቤትና ከመሳሰሉ መሠረታዊ ጥቅማጥቅሞች አኳያ እጅግ ብዙ ግፍ መቀበላቸው ይታወሳል።

አዋጁ ከተጻፈበትና በውስጡ ካካተተው መረጃ አንጻር ጥቅማጥቅሞቹ “ከጥልቅ ተሃድሶ” ጋር በተያያዘ በጡረታ እንዲገለሉ የሚደረጉ የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞችን አፍ ማስዘጊያ ሆኖ የቀረበ አንዱ “የጥልቅ ተሃድሶው” ውጤት ነው ተብሏል።

Source-gooulgul.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s