በሂውስተኑ ሙሉ ማራቶን መስከረም አሰፋ አሸነፈች | በወንዶች ግማሽ ማራቶን 2ኛ የወጣው ፈይሳ ሌሊሳ ዳግም እጆቹን ወደላይ በማጣመር የኢትዮጵያን ሕዝብ ብሶት አሰማ

በኦሎምፒክ መድረክ 2ኛ በመውጣት እጆቹን ወደላይ በማጣመር በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት ለዓለም ሕዝብ ያሳየው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ዛሬም በሂውስተን አሜሪካ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ 2ኛ በመውጣት ዳግም የሕዝብን ብሶት እጆቹን ወደላይ በማጣመር አሳይቷል::

በሂውስተን ግማሽ ማራቶን 2ኛ በመውጣት አኩሪ ተግባር የፈጸመው አትሌት ፈይሳ በቀጣይም ከቀነኒሳ በቀለ ጋር በአንድ መድረክ በለንደን ማራቶን ላይ ይገናኛሉ:: ቀነኒሳ በቀለ ፈይሳ ሌሊሳ በኦሎምፒክ መድረክ ከሕዝብ ጋር ቆሞ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የመብት ረገጣ ለዓለም ማሳየቱን መቃወሙ ይታወሳል::

ፈይሳና ቀነኒሳ የሚገናኙበት የለንደን ቨርጂን መኒ ማራቶን ኤፕሪል 23 እንደሚደረግ ቀን ተቆርጦለታል::

በሌላ በኩል በሂውስተን ዛሬ በተደረገው ሙሉ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መሰረት አሰፋ አንደኛ በመውጣት የሚያኮራ ውጤት አስመስዝግባለች:: ውድድሩን ለመጨረስ የፈጀባት ጊዜም 2:30:18 ነው::

በዚህ ውድድር ላይ ማሬ ዲባባ እና ት ዕግስት ቱፋ እንደሚወዳደሩ ቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ሳይሳተፉ ቀርተዋል::

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s