በነከድር መሃመድ መዝገብ እስከ 5 ዓመት የተፈረደባቸው 10 ሙስሊሞች ወደ ዝዋይ ተወሰዱ January 14,

ዘጋቢ አብዱረሂም አህመድ

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ጨምሮ በሱ መዝገብ የተከሰሱት 29 ኡስታዞችን ከእስር በሃይል ልታስፈቱ ነበር፣በታላቁ አንዋር መስጅድ እና በፒያሳ ኑር መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ ሲያደርገው በነበረው ተቃውሞ ተሳትፋችሃል፣ድምፃችን ይሰማ የሚል ወረቀት በትናቹሃል፣መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቱዋል ብላቹሃል በማለት በሃሰት የተከሰሱት የአዲስ አበባ እና የጅማ ወጣቶች የካንጋሮ ፍርድ ቤት ከ 4 አመት ከ5 ወር እስከ 5 አመት ከ6 ወራት በግፋ የፈረደባቸው 10 ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ ዙዋይ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸው ታወቀ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት 4 ወጣቶች፣በቅርቡ የተፈታው ጀግናው ኤልያስ ከድር ላይ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ ተጨማሪ ክስ በሃሰት መምስከር ክስ የተመሰረተበት እና ጉዳዩን በአራዳ ፍርድ ቤት እ ጀግናው ሙጂብ አሚኖ፣እና ሌሎች 3 ታሳሪዎች እዛው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መቅረታቸው የታወቀ ሲሆን ቀሪዎቹ 11 ወጣቶች ወደ ዙዋይ ማረሚያ ቤት መዘዋወራቸው ነው የታወቀው።

ወደ ዙዋይ የተዘዋወሩት 11 ወጣቶች እንደሚከተሉት ናቸው:–

1,ጋዜጠኛ ካሊድ መሀመድ
2,ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ
3,አብዱልሃሚድ መሀመድ
4,መሀመድ ኑሪ
5,ከድር መሀመድ
6,ሁሴን አሀመድ
7,ቶፍቅ ሚስበሃ
8,ሙሀመድ ከማል
9,ፉአድ አብዱልቃድ
10,ሀይሩ ኸይረዲን ።

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በግፍ ማረሚያ ቤቱ አቃጥላቹሃል በማለት የተከሰሱት እና በአሁን ሰአት በጨለማ ቤት የሚገኙት በቅርቡ ከቂሊንጦ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይዘዋወራቱ ተብለው ሚጠበቁት በአሁን ሰአት በቂሊንጦ የሚገኙት:–
1,ኢብራሂም ካሚል
2,ሻቡዲን ነስሩ
3,ፍፁም ቸርነት
4,ኡስማን መሀመድ
በነ ኤልያስ ከድር ላይ በሃሰት አልመሰክርም በማለቱ በሃሰት ምስክርነት በመስጠት ተጨማሪ ክስ በአራዳ ፍርድ ቤት የተመሰረተበት እና በአሁን ሰአት በቂሊንጦ ሚገኘው እና በቅርብ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይዘዋወራል ተብሎ የሚጠበቀው ሙጂብ አሚኖ በቂሊንጦ እንዲቆይ ተደርጉዋል

እንዲሁም ከሸዋሮ ቢት ሲመለስ ወደ ቃሊቲ ቀጥታ የተዟዟረው የጅማው ጀግና ወጣት ነዚፍ ተማም በቃሊቲ እንደሚገኘ ነው የታወቀው ጀግናው ሃሽም አብደላን ጨምሮ ቀሪ 2 ወጣቶች ደግሞ በዛው ቂሊንጦ እንደሚገኙ ነው የታወቀው እነርሱም

1,ሀሺም አብደላ
2,አብዱልሀፉዝ ሻፊ
3,አብዱልጀባር አብደላ

በሌላ በኩል ከ3 አመት ከ3 ወር እስከ 3 አመት ከ11 ወር የተፈረደባቸው በጀግነው ነብዩ ሲራጅ መዝገብ የተከሰሱ 7 ወጣቶች ወደ ዙዋይ ይዘዋወሩ አይዟዟሩ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ቢቢኤንም አጣርቶ ይፋ እንደሚያደርግ ለመግለፅ ይወዳል
ወደ ዙዋይ የተዟዟሩት 10 ወጣቶች ከቂሊንጦ ሲወጡ የሌላ እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ በእንባ እየተራጩ አሸኛኘት እንዳደረጉላቸው የታወቀ ሲሆን በዙዋይ የሚገኙት በነ አማን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ እና ሌሎች ሙስሊሞች ጨምሮ ለወጣቶቹ እንኳን የደህና መጣቹህ ፕሮግራም በማድረግ እንደተቀበሏቸው ነው የታወቀው

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s