አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስት ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃ በትንሹ 97 ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008)

አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃ በትንሹ 97 ሰዎች መገደላቸውን ሰኞ ገለጠ።

በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ተከፍቷል ባለው በዚሁ የተኩስ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎች መጎዳታቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

የብሪታኒያው የማሰራጫ ጣቢያ (ቢቢሲ) በአፍሪካ ፕሮግራሙ ሰኞ ባቀረበው ልዩ የቀጥታ ስርጭት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ያወጣውን ሪፖርት በመጥቀስ ዘገባን ያቀረበ ሲሆን፣ በባህር ዳር ከተማ በአንድ ቀን ብቻ በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን አመልክቷል።

በመቶዎችይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከመደበኛ እስር ቤቶች ውጭ ለእስር መዳረጋቸውን ያስታወቀው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ የሚደንቅ አይደለም ሲሉ የገለጹት የድርጅቱ የአፍሪካ ሃላፊ ሚቼሊ ካጋሪ፣ መንግስት እየቀረበበት ያለን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አውስተዋል።

ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ይኸው ግድያ በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ለድርጊቱ ተጠያቄ የሆኑ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሃልፊዋ አክለው ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እየቀረበበት ያለን መጠነ ሰፊ ተቃውሞ በውጭ በሚገኙ የሽብርተኛ ሃይሎች የተቀነበባረ ነው ሲል ምክንያት በመስጠት ላይ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s