በጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጥሎ የግልና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ አለመጀመራቸው ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 2 ፥ 2008)

ላለፉት ሶስት ቀናቶች በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ሰኞ ድረስ እልባት አለማግኘቱንና በከተማዋ የግልና የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራ አለመጀመራቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የፈጸሙትን ግድያ በመቃወም ነዋሪዎች በሶሮቃ አካባቢ አሁንም ድረስ ከመከላከያ አባላት ጋር ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።

ተጨማሪ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወደ አካባቢው በመስፈር ላይ መሆኑን የተናገሩት እማኞች በጎንደር ከተማ ቀይ ኮፍያ መለዮ ያደረጉ የጸጥታ ሃይሎች በመዘዋወር ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በከተማዋ ያለው ውጥረት አለመርገቡን ተከትሎም የማህበራዊ ዋስትና ተቋማት ለጡረተኞች ሊሰጡ የነበረን ወርሃዊ ክፍያ “ገንዘብ የለም” በማለት ሳይከፍሏቸው እንደቀሩ እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ገልጸዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱ በመጠየቅ ላይ ሲሆኑ የዞን አስተዳዳሪዎች ህዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል የተለያዩ ማግባባቶችን እያካሄዱ መሆኑንም ከነዋሪዎች ጋር ከተደረገ ቃለ-ምልልስ ለመረዳት ተችሏል።

የአማራ ክልል መንግስት በበኩሉ እሁድ በባህርዳር ከተማ ተካሄዶ በነበረ ህዝባዊ ተቃውሞ በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ሰኞ አስታውቀዋል።

Posted by-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s