አስገዳጁ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከነገ በስቲያ ጀምሮ ይካሄዳል ተባለ

Bilderesultat for ethiopian birthday party

ኢሃዲግ በሠሞኑ በኦሮሚያና በጎንደር የተነሣበትን ዉጥረት ለማርገብ አስቸካይ  የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት ምዝገባዎች በመላው አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች  አስገዳጅ መመዝገብና ማስመዝገብ ከነገ ወዲያ እንደሚጀመር አሣሠቡ፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ማብሰሪያ መድረክ ላይ ተገኝተን እንደሰማነው ከነገ በስቲያ የሚጀመረው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስገዳጅ በመሆኑ የማያስመዘግቡትና የማይመዘገቡት የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ጋብቻ፣ ሞትና ፍቺ ከተፈፀሙ በ30 ቀኖች ውስጥ ልደት ደግሞ በ90 ቀኖች ውስጥ መመዝገብ አለበት ተብሏል፡፡

በተጠቀሱት ቀኖች ያልተመዘገበ ወሳኝ ኩነት አጥጋቢ ምክንያት እስካልቀረበበት ድረስ ያስቀጣል መባሉንም በዝግጅቱ ላይ ሰምተናል፡፡

Bilderesultat for ethiopian weeding image

ምዝገባው ለዜጐች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ጠቀሜታቸው የጐላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት የሚባሉት ወሳኝ ኩነቶች አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ ድጋሚ ማስመዝገብ አይቻልም፡፡

የወሳኝ ኩነቶችን አለማስመዝገብ ከ6 ወር ያልበለጠ እሥራትና ከ500 እስከ 5 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ሲሆን ትክክለኛውን መረጃ አለመስጠት ደግሞ እስከ 5 አመት እሥራት ያስቀጣል፡፡

ሐሰተኛ የምዝገባ ሰርተፍኬት ይዞ መገኘት ከ7 እስከ 15 ዓመት እሥራት ያስቀጣል ተብሏል፡፡

ከነገ በስቲያ ጀምሮ የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት ምዝገባዎች በመላው አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ስለሚካሄድ መመዝገብና ማስመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

በውጭ ሀገር የሚኖር ዜጐች በኤንባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች መመዝገብ ይችላሉ የተባለ ሲሆን የአገር መከላከያ ሚኒስቴርም በሥራ ላይ ሳሉ ህይወታቸው የሚያልፍ አባሎቹን እንደሚመዘግብ ተነግሯል፡፡

ለመጪዎቹ አምስት አመታትም ለምዝገባዎቹ ከ246 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ሲባል ሰምተናል፡፡

በኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን ለመጀመር ጥረት የተደረገው ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የነበረ ሲሆን የሀገሪቱ ህግ አካል ሆኖ የተደነገገው በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐ-ብሔር ህግ ነው፡፡

ይሁንና ላለፉት በርካታ አመታት ከልማዳዊ አሰራር የተላቀቀና አስፈላጊውን ደረጃ ያሟላ የምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ አለመቻሉን ሰምተናል፡፡

ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባውን ያበሰሩት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የሀገሪቱ ዜጐች ለምዝገባው ቀና ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

Posted  By/Lemlem Kebede

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s