በአማሪካ ያልተሳካላቸውን የቲዎክራሲ የመንግስት ምስረታ በኢትዮጵያ በአሻንጉሊት አመራር በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለመግዛት ሮኒ ፍሎይድና እብሪተኛ ግብረ አበሮቹ በሃይማኖት ሰበብ ብቅ ሊሉ ነው

 

ኢትዮጵያን በ50000 ቤተ እምነት አጥለቀልቃለሁ ባዮ ሮኒ ፍሎይድና እብሪተኛ ግብረ አበሮቹ ምን ጊዜም ቢሆን ሐይማኖት የፖለቲካ መሳሪያቸው መሆኑን አይደብቁም። በፎክስ የቴሌቪዢን ጣቢያ ሬኒ ራሱ ካለኛ ፈቃድ ለአሜሪካ እንኳን ፕሬዚደንት ሊመረጥ አይችልም ብሎ ተከራካሪ ነበር። ፕሬዚደንት ኦባማ እንዳይመረጥ የማያቋርጥ ጥረት ቢያደርግም የአሜሪካ ህዝብ በተደጋጋሚ አሳፍሮታል። በአሁኑም የምርጫ ውድድር የለከተ ቢሱ ዶናልድ ትረምፕ አቀንቃኝና የሽምቅ ተዋጊ ነው። አሁንም ቢሆን የአሜሪካ ሕዝብ ደግሞ እንዳያሳፍረው ግልጽ ነው።

ሮኒ በአሜሪካ በተደጋጋሚ አልሆን ሲለው ፤ እድሉን ለማሻሻል አይኑን ወደ አገራችን ኢትዮጵያ አዙሯል። ለእሱና ግብረ አበሮቹ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የእሱ ዘርማንዘር እንጨት በሚያመልክበት ዘመን ክርስትናን የቱቀበለች ብትሆንም ፤ እምነታችን ከንቱ ነው ብለው ስለሚቆጥሩ ፤ በኢትዮጵያ ክርስቲያን አለ ብለውም አይቆጥሩም። ይህ አስተሳሰብ የሙሶሎኒና ግብረ አበሮቹ ፋሺስቶችም አስተሳሰብ ነበር። ለሮኒ ኢትዮጵያ የሐይማኖት ቅኝ ለመሆን የተዘጋጀች አገር ናት። እንደ እሱና አቀንቃኞቹ አስተሳሰብ የተዋህዶን ሐይማኖት ከምድረ ገጽ ማጥፋትና በነሱ ሐይማኖት መተካት ዋናው አላማቸው ነው። ቢሆንላቸው ቤተክርስቲያኖቻችንን ንዋየ ቅዱሳኖቻችንን ከምረው ቢያቃጥሉ ደስታቸው ነው። የረጅም ጊዜ አላማቸውም በአማሪካ ያልተሳካላቸውን የቲዎክራሲ የመንግስት ምስረታ በኢትዮጵያ በአሻንጉሊት አመራር በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለመግዛት ነው። እነዚህ መሰሪዎች ቢቻላቸው ለጥቅማቸው የሚያመቻቸው ከመሰላቸው በሐይማኖት ጦርነት ብንተላለቅ ደስታውን አይችሉትም። ከአረብ አገር አክራሪነት እንዳይመጣና ሰላማችንን እንዳያደፈርስ ስንፈራ ፤ አሁን ግን በተንኮል የተራቀቁ ነጭ ምስጦች ባለፉት የቅኝ ዘመናት ያልተሳካላቸውን መሰሪነት በጠራራ ፀሐይ በድፍረትና በንቀት ይዘውብን ቀርበዋል።

ወገኖቼ ይህትልቅ አደጋ ስለ ሆነ በጥብቅ ጸልዮበት ፤ በየሰበካው ተወያዩበት ፤ ለማያውቁ አሳውቁ። በተለይ የሐይማኖት አባቶች የቀድሞ አባቶቻችሁን ምሳሌ ተከትላችሁ ስለ መጣው አደጋ አስተምሩ። ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅልን ፤ ሮኒ ፍሎይድና ሳንደርስባቸው የደረሱብንን እኩያት እግዚአብሔር በተለመደው ክንዱ ይምታቸው።

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s