የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በታች እንደሚያሽቆለቁል አይ.ኤም.ኤፍ. አስታወቀ

ሚያዚያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በምህጻረ ቃሉ አይ ኤም ኤፍ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት በያዝነው ዓመት ላይ የኤኮኖሚ እድገታቸው እንደ ሚያሽቆለቁል ገልጾአል፡፡
ድርጅቱ ድርቁን ተከትሎ ኤኮኖሚያቸው ክፉኛ ከሚጠቁ አገራት ተርታ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ተጎጂ አገር መሆኗንና ካለፈው ዓመት ካስመዘገበችው እድገት ከግማሽ በታች በመውረድ 4.5% ከመቶ እንደምታስመዘግብ ገልጾአል፡፡
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የነዳጅ ላኪ የአፍሪካ አገራት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ግሽበትን ተከትሎ በኤኮኖሚያቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳርፍባቸው አይ.ኤም.ኤፍ. አመልክቶ አንጎላና ናይጀሪያ ከተጎጂዎቹ አገራት ተርታ ተቀምጠዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ቀደም ብሎ ድርቁን ተከትሎ የሚመጣ የኤኮኖሚ ውድቀት እንደማይኖር ሲገልጹ የነበረ። በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስቴር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ 7% ከመቶ እድገት እንደሚጠበቅ የተናገሩ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ የኤኮኖሚ አማካሪ አርከበ እቁባይ በበኩላቸው 11% ከመቶ ኤኮኖሚያዊ እድገት ይመዘገባል ማለታቸው ይታወሳል። የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ድርቁ በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ተጽኖ አይኖርም ብለው የተናገሩ ሲሆን፣ ለዚህም የሰጡት ምክንያት፣ በድርቅ የተጠቃው አካባቢ የአርብቶ አደሩ አካባቢና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የጎላ አስተዋጽኦ የማያደርገው ክፍል ነው የሚል ነበር፡፡

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s