ብቸኛው የትግራይ ወያኔ አገዛዝ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ (ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ)

አንድ ነገር ከተለያዩ ነገሮች የዉህደት ዉጤት መሆኑን የምናዉቀው እነዚያ በቀመሩ ላይ የተቀመጡት የተለያዩ ነገሮች በተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው በውህደቱ ዉስጥ ተግባራዊ የሆነ መንስኤአዊና ክትትልነት ያለው ከዉጭ ከምናየው መጠናዊ የቅምር መሰረት ስራ ሲሰሩ ነው፣ ያ ካልሆነ ግን ዉህደቱ ትክክለኛ ጥምረት ሳይሆን ለይስሙላ ብቻ ያሉ ግን በተግባር የሌሉና ስብስቡም የአንድ ነገር ስብስብ ብቻ ነው። ለምሳሌ የምንጠጣው ዉሃ የ 2 እጅ ሃይድሮጅን እና 1 እጅ ኦክስጅን ዉህደት ዉጤት ነው እነዚህ ሁለት ነገሮች ተፈላጊዉን የንጥረ ነገር ስራ ይሰራሉ፣ ከሁለቱ ነገሮች ትንሽም የሆነ ክፍል ከጎደለ ዉሃ የለም፣ ስለዚህ ነገሩ ኦክሲጅን ነው ወይም ሃይድሮጅን።

በኢትዮጵያ ዉስጥ ላለፉት 25 አመታት የትግራይ ወያኔ ቡድን ከደደቢት ዋሻ እንደ አዉሬ በርግጎ ወጥቶ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተው ታሪካዊ አደጋና አጋጣሚ ስልጣን ላይ ወጥቶ ሃገራችን ኢትዮጵያን አንቆ ይዞ ምንም አይነት ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ በሌለውና ከቦኒቶ ሞሶሎኒ በበለጠ ሁኔታ መሰረቷን በማናጋትና ማንነቷን እያፈረሰ፣ ህዝቦቿን እጅግ በጣም ኋላ ቀር በሆነና የአለም ህዝቦች ጥለዉት በሄዱት አሳፋሪ የጎሳ ድሪቶ እርስ በርሳቸው እያናቆረና እያገዳደለ ብቸኛው ተጠቃሚ አውሬ ሆኖ ለመኖር በየመንደሩ ለቃቅሞ ለሱ የሚያገለግሉ እንስሳዊ ፍላጎት ብቻ ያላቸዉን ግለሰቦች የጥቃቱ ሰለባ በሆነበት ህዝብ ዉስጥ መልምሎ የስልጣን ተጋሪ ድርጅቶች ናቸው ብሎ ለይስሙላ፣ በተግባር ግን ወያኔ ብቻ የሚመራውን አገር አቀፍ የዝርፊያ ድርጅቱን በየቦታው መሰረተ።
እነዚህ ግለሰቦች ያንተ ተወካዮች ናቸው እከሌ የሚባል ያንተን ጎሳ ስም የያዘ ቡድን ታርጋ ተሰጥቷቸዋል የናንተን አባልነት ይጠይቃሉ፣እናንተም ችግራችሁን ለነዚህ ተወካዮቻችሁ ታቀርባላችሁ በዚያም መሰረት መፍትሄወች ይፈለጋሉ እያለ፣ ለዚህ ሃገራዊ ወንጀል ተባባሪ እንዲሆኑ የሰበሰባቸዉን ግለሰቦችም የፈለጉትን ነገር እንዲዘርፉ ማስቻል፣በዚህም እጅግ መጠን ያጣ ሃገራዊ ስሜት በሌለው መልኩ የህገወጥነትና ዘራፊነት ስርአት ተመስርቶና ተንደላቆ ለመኖር የወያኔን ወንጀል በመደበቅና በፊርማቸውም ተባባሪ በመሆን እስካሁን ድረስ አሉ።

ከነዚህ የወያኔ የይስሙላ ድርጅቶች ዉስጥ አንደኛው የእንስሳ ስብስብ አማራዉን እንዲወክል ብአዴን የሚል ታርጋ ተሰጥቶት የአማራ ህዝብ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ ቢሮ ይዞ ያለው ቡድን ነው። ይህ ቡድን ለአማራ ህዝቦች ተወካይና ተቆርቋሪ ሳይሆነ የአማራን ህዝብ ቤቱ ዉስጥ ሆኖ ለማሸበር፣ በጎጥ ለማበጣበጥና ባልና ሚስትን ለማገዳደል፣ ለማፈን፣ ለማሰርና ለመግደል፣ የወያኔን ወንጀል ህዝቡ እንዳያይ፣ አይንህን ጨፍን ዝም ብለህ ኑር እንዲል ተልኮ የተሰጠው የትግራይ ወያኔ የመዋጊያ ድሪቶ ነው ። በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል በጎንደር አማራው በጎሳው ብቻ ይህ ነው የሚባል ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊና ማህበራዊ ጥቃት ሲፈጸምበት አንድም ነገር ተናግሮ የማያውቅ ግን ለዚያ ወንጀል ተባባሪ ሆኖ ከወያኔ ጋር የሚጨፍርና ይባስም ብሎ የሚሳደብ ድርጅት ፣ የጎንደር አካል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ህገወጥ በሆነ መልኩ ማንነቱ ተጨፍልቆ፣ መሬቱም ከጎንደር ተለይቶ ወደ ትግራይ ተወስዶ ለሁልት አስርተ አመአታት በበደል፣ በስቃይ፣ በመገደልና በመሰደድ ፣ ከዚአም የተረፉት ቋንቋቸውን አትናገሩ ትግርኛ ቋንቋ ተማሩ እየተባሉ ኢሰብአዊ በሆነ አያያዝ እየኖሩ ከነሱ ጋር እየኖረ ምንም ያላለ ድርጅት ነው።

ይህ የድሪቶ ድርጅት ከጎናቸው እያለ የናንተ ተወካይ ነኝ እያለ ፣ የትግራይ ወያኔ የተከዜን ወንዝ እያቋረጠ በየቀኑ ጎንደር ዉስጥ ጎንደርን የማፍረስ ስብሰባ እያካሄደ፣ ምንም አይነት የአማራዉን ህዝብ ተወካይነንት የያዘ ስሜት ሳያስይና ተግባር ሳይፈጽም ግን ለወያኔ የተቀጠረ የደህንነትና የጥበቃ ስራ ብቻ ለመስራት እንደሚኖር ህዝቡ አይቷል አውቋልም።አንድም ጊዜ የትግራይን ወያኔ ለምንድነው ይህ ህዝብ አማራ ነኝ እያለ ነው፣ እኛም እናውቃለን፣ ይህ ህዝብ በታሪክም በስነ ልቦናም ሁልጊዜ የጎንደር አካል እንጅ የትግራይ ሆኖ አያዉቅምና ትክክለኛ የሆነ መፍትሄ መፈለግ አለብን፣ ማንነታቸው መመለስ አለበት፣ መሬቱም ወደጎንደር መመለስ አለበት እንደማለት ፋንታ፤ አይ ዝም በሉ፣ እኛ የምንወያየው ስለምትኖሩባት መንደርና አካባቢ ብቻ ነው፣ ስለወልቃይት ጠገዴ አታንሱ መልስም የለንም እያለ (እዉነት ነው መልስም የላቸዉም ምክንያቱም የወያኔ የቁጭበሉ የጎሳ ታርጋ ያዞች ናቸዋ) የህዝቡን ቁጭትና ብሶት በማፈን ስራ ላይ ተሰማርቶ ያለ የወያኔ ተወካይ መሆኑን ነው። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ይህን የረጅም ጊዜ በደሉን ለማሰማት በየቦታው ቢጮህም ሰሚ አጥቶ አሁን በመጨረሻ ብቸኛው አዲስ አበባ ላይ ያለው የትግራይ ወያኔ (ግን ብሄራዊ) ሸንጎ ጥያቄአችሁን የትግራይ ቡድን ነው የሚመለከተው ብሎ ወደመንደሩ ተመልሳችሁ ሂዱ ብሎ ወሰነባቸው፣ ማለትም እናተ የትግራይ አካል ናችሁ፣ ችግራችሁንም እኔ ለማስተዳድረው ለክልላዊ መንግስታችሁ ጠይቁ እዚህ የናንተን ችግር የምናይበት(የማይበት) ምክንያት የለም ነው።

ይህ ፍርድ የሚያረጋግጠው አንድ ነገር ብቻ ነው አዲስ አበባ ያለው ሸንጎ የትግራይ ወያኔ ያቋቋመው የሌሎች ጎሳወች ውክልና በታርጋ ብቻ የሆነበት ወያኔ ብቻ የሚቆጣጠረውና የሚያዘው የሌባ ሸንጎ መሆኑን ነው። እዚህም እኔ ነኝ እዚያም እኔ ነኝ ስለዚህ ወደዚያ እኔ በስሜና በተግባሬ በግልጽ በምታወቅበት ቦታ ሂዱ ነው ያለው። ማንም ሰው ያውቀዋል ከሌባ ምንም ፍትህ አይጠበቅም፤ ፍትህ መስረቅን ማጭበረበርን እንደዋነኛ የመተዳደሪያ ባህሪ አድርጎ ከያዘ ሰው ወይም ድርጅት መጠበቅ የዋህነት ነው፣ ፍትህ የእዉነተኛ ሰው ወይም ድርጅት የእዉነታዊ ባህሪ ተግባራዊ ነጸብራቅ ነችና።

ጀግናው የጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ግን ማንነታችን፣ ርስታችን ፣ የተወለድንበትን, ያደግንበትን, አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን ጠብቀው ያቆዩልንን ክልል በዚህ የወያኔ ቁጭ በሉ ሸንጎ ድለላ ሳንዘናጋ ለማስከበርና ለማስመለስ ትግሉን በበለጠና ዉስብስብ በሆነ ስልታዊ መልኩ መቀጠል አለብን። የትግራይ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት መንገሻ ስዩም እንኳን በቅርቡ የትግራይ ወሰን ተከዜ እንደሆነ እራሳቸዉም እንደሚያውቁ ፣ ከአባታቸውም ከዚያ በፊትም ከቅድመ አያቶቻቸውና በታሪክም የሚያውቁት ይህንኑ እንደሆነ ተናግረዋል ፣ ወያኔ በቅሌት የሰዉን እርስት ሰርቆ፣ አይነጋም መስሏት ከምትተኛበት ላይ … እንደሚባለው የሰረቀዉን መሬት ይዞ ለመቅረትና ለማወናበድ የፈለገዉን አፈር ቢቆፍር ታሪክንና እዉነትን ማዳፈን አልቻለም፣ አይችልምም ። የኢትዮጵያ ታሪክ በጽሁፍ ላይ መስፈር ከጀመረበት፣ የሰው ልጅ የመሬትን ገጸ ባህሪ ካርታ ላይ በመዛግብት ማዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የምናዉቀውና ሁሉም የአለም ህዝብ ከታሪካዊ ሙዚየማቸው የሚያዩት ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የጎንደር አካል እንደነበረና፣ ጎንደርና ትግራይ አዋሳኝ የሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደነበሩ፣ ወሰናቸዉም አንጋፋው የተፈጥሮው ወንዝ ተከዜ መሆኑን ብቻ ነው።

የትግራይ ወያኔ ቡድን ይሀንን ዘላለማዊ ማህበራዊና ታሪካዊ እዉነታን ነው በጉልበትና በማን አለብኝነት አፍርሶ አሁንም ጥፋቱን ከማመንና ይቅርታ ከመጠይቅ ይልቅ በጉልበት የሰዉን ንብረት እንደሰረቁ ልኑር የሚለው፤ አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሞ ጤነኛ የሆነ ዘላቂነት ያለው ግኑኙነት, ወንጀል ከተፈጸመበት አካል ጋር ሊመሰርት አይችልም ፤ ያ የሚሆነው መጀመሪያ ወንጀል መፈጸሙን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ሲችልና ተበዳዩ ክፍል ይቅርታዉን አምኖበት ሲቀበለው፣ ከዚያም የፈጸመዉን ወንጀል አምኖ መመለስ፣ ካልሆነ ደግም ካሳ መክፈል ሲችል ነው። ወያኔ ግን የፈለጉትን ወንጀል እየሰራሁ ከማንም የኢትዮጵያ ህዝብ ጎረቤት ሆኘ መኖር እችላለሁ ስለሆነ የኑሮው ፍልስፍና፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ፍጹም ማሰብ የተሳነውን የእንስሳ ቡድን በተናጠል ሳይሆን በተባበረ መልኩ ማጥፋት አማራጭ የሌለው ተግባሩ መሆን አለበት። ዘመናዊ ለሆነ ሰው የአንድ አመት ነጻነት ከእድሜ ልክ ባርነት እጅግ እጅግ ይሻላል። አሜሪካ ዉስጥ የሰዉን ማንነትና የመኖርን ትርጉም ዋጋ የሚያሰጠው ፣ እንደ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የምንወደው አንድ አባባል አለ ” ነጻነቴን ስጠኝ ወይም ሞቴን” ነጻነት ከሁሉም በላይ እንደሆነና ፣ ዝም ብሎ ህሊናን ሽጦ ግኡዛዊ ህይዎትን ለመግፋትና ሆድን ለመሙላት ብቻ መኖር ግን የእንስሳ ብቸኛው ፍላጎትም ችሎታም ነው።

ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁበጆን ታይለር ኮሙኒቲ ኮለጅ ቨርጅኒያ ሀገረግዛት አሜሪካ የሂሳብ አድጃንክት ፕሮፌሰር ናቸው、

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s