የእንግሊዝ ፓርላማ የአንዳርጋቸውን ጉዳይ በዝርዝርና በጥልቀት ላየው ነው አለ

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በውጪ አገራት በእስር ላይ የሚገኙ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን (በኢትዮጵያ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ) እስረኞች ጉዳይ በማጥናት መንግስት በውጪ አገራት በሚገኙ እንግሊዛዊያን ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ረገጣን ለማስቀረት የሚያሳየውን ቁርጠኝነት እመዝናለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ትናንት ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነም ብዛት ያላቸው እንግሊዛዊያን በውጪ አገራት ታስረው የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ሲፈጸምባቸው መንግስት የሚጠበቅበትን ጫና በማሳረፍ ዜጎቹን ከሚደርስባቸው ጥቃት መከላከል አልቻለም፡፡ባለፈው ዓመት የነሐሴ ወር የወጣን ሪፖርት ኮሚቴው መመልከቱ የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አገራት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ግድ የማይሰጠው መሆኑን ታዝበዋል ተብሏል፡፡

በፓርላማው የተዋቀረው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በመንግስት የሰብዓዊ መብት አከባበር ስራ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግ በመግለጽ በውጪ አገራት የሚገኙ እንግሊዛዊያን እየደረሰባቸው የሚገኝን የመብት ጥሰት በዝርዝርና በጥልቀት በመመልከት የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር መንግስት የተጓዘውን ርቀት እንደሚቃኝ አውስቷል፡፡

በለንደን የአንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመርዳት ላይ የሚገኘው ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነም የፓርላማ ቡድኑ በዋናነት የአቶ አንዳጋቸውን ጉዳይ መመርመር ይጀምራል፡፡

አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጪ መያዛቸውን በመቃወም የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ፓርላማ አንዳርጋቸውን ኢትዮጵያ በነጻ እንድትለቅ ሲጠይቁ የእንግሊዝ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ሳያቀርብ በመቆየቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ሪፕራይቭ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ዋነኛው ደጋፍ አድራጊ መሆኑን ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ ሪፕራይቭ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s