የሰው ልብና ጉበት የሚበላው ሽብርተኛ ወደ ሲኦል ተላከ

alnasra

በሶሪያ የአል ኑስራ አሸባሪ ቡድን ከፍተኛ መሪ የነበረውና  የተገደለን የሶሪያ ወታደር ልብና ጉበት በመብላቱ የሚታወቀው  ካሊድ አቡ ሳቃር በአየር ድብደባ መገደሉን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡

አቡ ሳቃር አል ኑሳራ የተባለውን ቡድን ከመቀላቀሉ አስቀድሞ የአል ፋሩቅ ብርጌድ አመራር እንደነበር ይነገራል፡፡ከሶስት ዓመታት በፊት ሳቃር በሶሪያ ሆምስ አውራጃ አንድ በጦርነት የተገደለን የሶሪያ መንግስት ወታደርን ልብና ጉበት ሲመገብ በተቀረጸ ቪዲዩ በመታየቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በጭካኔው ለመታወቅ በቅቷል፡፡

የሩሲያ ተዋጊ ጄቶች በሶሪያ ሰሜናዊ ምዕራብ በምትገኘው ኢድሊብ ባደረጉት ድብደባ የአል ኑስራን ቃል አቀባይ ጨምሮ 19 የቡድኑን አባላት መግደላቸው ታውቋል፡፡

የሶሪያና የሩሲያ አየር ኃይሎች በስለላ ሰራተኞቻቸው አማካኝነት የሽብርተኛው ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ለስብሰባ መቀመጣቸውን ከደረሱበት በኋላ ድብደባውን መፈጸማቸው ተነግሯል፡፡ በድብደባው ሶሪያዊያን ያልሆኑ የሌላ አገር ተወላጅ የሽብርተኛው ቡድን ኮማንደሮች መገደላቸውና ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ መቁሰላቸው ተወስቷል፡፡

አቡ ሳቃር ከቡድኑ አመራሮች ግምባር ቀደሙ ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡በ1970ዎቹ አል ቃይዳን በመደገፍ በአፍጋኒስታን ጦርነት መሳተፉ የሚነገርለት አቡ ሳቃር ከአልቃይዳው የቀድሞ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ነበረውም ተብሏል፡፡

ምንጭ ኢስላሚክኢንቪቴሽን

 Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s