ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብም ልትጠቀም ነው

ኢትዮጵያ የጂቡቲ ወደብ በመጨናነቁ ምክንያት በድርቅ ለተጎዱት ዜጎችዋ ባዘጋጀችው የርዳታ እህል እና በሌላ የንግድ እንቅስቃሴዋ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል ስትል በበርበራ ወደብ ለመጠቀም ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት መፈራረሟ ተሰማ። አንዳንድ የዜና ምንጮች የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የኤኮኖሚ እና ንግድ አማካሪ ሻርማርኬ ጃማን ጠቅሰው በድረ ገፆቻቸው እንደዘገቡት፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነቱን የተፈራረሙት ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ነው። ሁለቱ ሀገራት የስምምነቱን ገቢራዊነት የሚያመቻች አንድ የጋራ ኮሚቴ አቋቁመው በመስራት ላይ መሆናቸውንም የወጡት ዘገባዎች አስረድተዋል። ኢትዮጵያ  ከጠቅላላ የንግድ እንቅስቃሴዋ መካከል 30% እስካለፈው ሐምሌ ወር ድረስ በበርበራ ወደብ በኩል እንዲያልፍ እጎአ በ2015 ዓም ባወጣችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድዋ ወስና እንደነበር ዘገባዎቹ አስታውሰዋል፣ ይሁንና፣ በበርበራ የወደብ ይዞታ እና ወደብ ከተማይቱን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያገናኙት መንገዶች ሁኔታ የተነሳ  97% ንግዷ አሁንም በጅቡቲ በኩል ማለፍ እንዳለበት፣  እንዲሁም፣  ለሰሜን ኢትዮጵያ የታሰበ ማዳበሪያ በፖርት ሱዳን በኩል መቀበል እንደጀመረችም የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚንስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ማስረዳታቸውን የዜና ምንጮቹ ገልጸዋል።

Source-dw.de.com

Posted By-Lemlem Kedede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s