ፍርድ ቤቱ የአላሙዲ ድርጅት 433.571.241 ብር እንዲቀጣ ወሰነ

በእንግሊዘኛ ቋንቋ በየሳምንቱ በኢትዮጵያ እየታተመ የሚሰራጨው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው በአራት የመንግስት ኢንተርፕራይዞች ሽያጭና ግዢ ሁለት ክሶች የቀረበበት ሜድሮክ ከእህት ካምፓኒዎቹ አንዱ ሆሪዞን ፕላንቴሽን የግል ካምፓኒ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲዘጋና የተወዘፈበትን የግማሽ ቢልዩን ብር ዕዳ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ኢንተርፕራይዝ እንዲከፍል ተወሰነበት::

alamudi ethiopia

 

 

 

 

 

 

 

 

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ጎጀብ የእርሻ ልማት፣ሆሪዞን አዲስ ጎማ፣ሊሙ የቡና እርሻና በበቃ ቡና የተባሉት ድርጅቶች ለሜድሮክ በመሸጣቸው የቅድመ ክፍያ ተፈጽሞና ሙሉ ክፍያቸው የሚፈጸምበት ጊዜ በውል ስምምነቱ ተጠቅሶ ንብረቶቹ እንዲዘዋወሩ ተደርገው ነበር፡፡

ጋዜጣው አያይዞም ሆሪዞን ፕላንቴሽን በውሉ ሰፍሮ የነበረውን የክፍያ ጊዜ መከተል ያልቻለው ባስተናገደው የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሆሪዞን በበኩሉ የስድስት ወራት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠውና በሁሉም ጉዳዩች የተፈጠረውን ስህተት ለማስረዳት እንዲችል ጠይቆ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛው ችሎት ለወራት ጉዳዩን ሲመለከት መቆየቱን በማስታወስ ሁለቱ ካምፓኒዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ሳይቀበል ቀርቷል ያለው ጋዜጣው በአጠቃላይ የቢልየነሩ ሼህ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሜድሮክ እንዲከፍል የሚጠበቀው እዳ 433.571.241 ብር ስለመሆኑ ከቀረበበት ክስና ከተሰጠው ውሳኔ መረዳት ተችሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተላለፈው ውሳኔ በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ሳይፈጸም ከቀረም ጥቅሙ እየተሰላ የብሩ መጠን እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን አዲስ ፎርቹን ዘግቧል::

Posted By- Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s