በኦሮሚያ በአርሲና ኤሊባቡር የተማሪዎች ተቃውሞ አገርሽቷል – በምዕራብ ሐረርጌም ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው

oromo st

ጋብ ያለ መስሎ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ እንደአዲስ በየቦታው እያገረሸ መሆኑ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የሚደርሰው መረጃ ጠቆሙ::

በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች እንደአዲስ ተቃውሞው ያገረሸባቸው አካባቢዎች ኢሊባቡር; ሐረርጌ እና አርሲ ናቸው:: በምዕራብ ሐረርጌ ፋዴስ ወረዳ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የሰፈረው የሕወሓት ልዩ ኃይል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ተቃውሞውን እንዲያቆሙ እርምጃ ለመውሰድ ቢሞክርም የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ እንደሚገኝ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ:: የአካባቢው ነዋሪ የወረዳውን አስተዳደር ከስልጣን እንዳባረረውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

oromoበኤሊባቡርና አርሲም እንዲሁም ዳግም የሕዝቡ ቁጣ አይሎ ከሕወሓት ልዩ ኃይል ጋር ህዝቡ ተፋጦ እንደሚገኝ ተሰምቷል:: በኤሊባቡርና አርሲ የተለያዩ ከተሞች የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ እያካሄዱ የሚገኙት ተማሪዎች ናቸው ተብሏል::

በሌላ ዜና በኮፋሌ በተደረገ የህዝብ ተቃውሞ በሕወሓት ልዪ ኃይል ተመቶ ቁስለኛ የነበረው ወጣት አሊ ቡሪ ቀሬሶ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ:: በኮፋሌ ከተማ ሓዊ ሆቴል ውስጥ ሰራተኛ የነበረው ይኸው ወጣት የአጋዚ ወታደሮች ወደ ሆቴል በመምጣት ወጣቱን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎችን በተለይም ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን ለሆቴሉ ደንበኞች ታሳያለህ በሚል ክፉኛ ቀጥቅጠው አቁስለውታል:: በዚህም ጉዳት የደረሰበት ወጣት ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መጥቶ ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል:

 

 

 

Source-zehabesha.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s