በኦሮሚያ በየቦታው የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ ነው – ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራን” አሉ

 

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሥፍራዎች ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ:: ታክስ ሰብሳቢዎችም እንዲሁ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ግብር ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ሥራ መስራት እንደተቸገሩም ለማወቅ ተቻለ::

የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንዳመለከቱት በ አርሲ በባሌ በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ, በምስራቅ ሸዋ; በ ም ዕራብ ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ የአጋዚ ጦር አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ በየጫካው ሥር እንደሚገኙ ታውቋል””

በም ዕራብ ሸዋ አምቦ; አመያና ግንደበረት ባለፉት 3 ሳምንታት ብቻ ከ6 በላይ የአጋዚ ጦር አባላት ተገድለው ተገኝተዋል:: እንደ አይን እማኞች ገለጻ በግንደበረት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የአጋዚ ጦር አባላት ላይ ህዝቡ እርምጃ እንደወሰደም ታውቋል::
ከግንደበረት አካባቢ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም ህዝቡ ተፈትሮዋዊ ያልሆኑ ገደሎችን በመሥራት የአጋዚ ጦር መኪኖች ሲሄዱ እንዲገለበጡ በማድረግ ላይ እንዳለም ታውቋል::

በአሪሲ ሮቤ; መርቲ; ገደብ; እና ኮፈሌም እንዲሁ የአጋዚ ጦር አባላት እየሞቱ እየተገኙ ሲሆን መንግስት ግን ይህን ደብቆ እንደሚገኝ ታውቋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች ግብር ለመሰብሰብ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት አካላት ላይ ሕዝቡ ጥቃት በማድረሱ የተነሳ ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራነው ስለዚህ ሄደን ግብር ክፈሉ ማለት አንችልም” በማለት ሥራ እንዳቆሙ ለመረዳት ተችሏል:: ግብር ክፍሉ እያሉ በም ዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ የተንቀሳቀሱ የመንግስት አካላትን ሕዝቡ በቆመጥ ቀጥቅጦ እንዳባረረም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

ከም ዕራብ ወለጋ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም በተለይም በነጆ; በጃርሶና ጊምቢ አካባቢም ህዝቡ አድብቶ በመጠበቅ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል::

Posted By-Lemlem Kedede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s