በወልቃይት የወከባ ስሞታው እንደቀጠለ ነው

ወከባ የሚደርስባቸው አካባቢያቸው “ወደ ትግራይ መካለሉ አግባብ አይደለም፣ የእኛ ክልል አማራ ነው” የሚል ጥያቄ በማንሣታቸውና ጥያቄአቸውንም በፊርማ አስደግፈው ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ በመላካቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው።

ወደ ዝግጅት ክፍላችን ከወልቃይት የሚደውሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የተለያየ ገፅታ ያላቸው ጥቃትና ወከባ እየተፈፀመብን ነው እያሉ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ወከባ የሚደርስባቸው አካባቢያቸው “ወደ ትግራይ መካለሉ አግባብ አይደለም፣ የእኛ ክልል አማራ ነው” የሚል ጥያቄ በማንሣታቸውና ጥያቄአቸውንም በፊርማ አስደግፈው ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ በመላካቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው።

ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተጠሩ እንዲፈርሙ መደረጉ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን፤ ከየት እንደመጡ የማያውቋቸው ሰዎች አሁንም ሰዉን እያስፈራሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በተጨማሪም “የኪነት ቡድን ወደ አካባቢው እየላኩ በዘፈን ያስሰድቡናል፤ ያስፈራሩናል” ብለዋል።

ከአካባቢውና ከክልሉ ባለሥልጣናት ስለሁኔታው ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሣካም።

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የመሩት ከአራት ወረዳዎች የተወከሉ ስድስት መቶ ሰዎች የተሣተፉበት ጉባዔ ሰሞኑን በሁመራ አካባቢ የተካሄደ ሲሆን የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሐድስ ዘነበ ሲናገሩ “.. የሌለ ድርሰት – የማንነት ጥያቄ እያስነሱ እርስ በራሱ እንዲጫረስ፣ ከልማት ጎዳና ለማስወጣት እየሠሩ ይገኛሉ።” ብለዋል።

Source-voa.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s