የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ የ18 ሰዎች ሕይወት ጠፋ | 25 ሰዎች ተጎድተዋል

በኢትዮጵያ በየቀኑ የሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ብዙ አምራች ዜጋዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል:: በዘ-ሐበሻ ድረገጽ እንኳ በየጊዜው እየደጋገመን በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች የሚደርሱ የመኪና አደጋዎችን ስንዘግብ ቆይተናል:: ትናንት በአርሲ ዞን ጎለልቻ የደረሰው የመኪና አደጋም ከአስፈሪዎቹና አሳዛኞቹ የመኪና አደጋዎች መካከል አንዱ ነው::

ፎቶው የተገኘው: ከራድዮ ፋና

ፎቶው የተገኘው: ከራድዮ ፋና

በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው ራድዮ ፋና እንደዘገበው ትናንት ምሽት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ 200 ሜትር ጥልቀት ባለውና ጨነኒ ወንዝ አካባቢ ልዩ ስፍራው የተፈጥሮ ድልድይ የሚባለው ቦታ ገደል ውስጥ ገብቶ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል::

በዚህ አደጋ 25 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ቢደርስባቸውም ስድስት ተሳፋሪዎች ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መትረፋቸው ተዘግቧል::

በኢትዮጵያ ሹፌሮች ጫት ቅመው; መጠጥ ጠጥተው መኪና ይነዳሉ:: ሹፌሮች የትራፊክ ሕጉን ሳይሆን ፖሊስን ነው የሚፈሩት:: ይህም ማለት ትራፊክ ፖሊሶች ባሉባቸው አካባቢዎች ብዙ ጉዳት አይፈጠርም:: ሆኖም ህግን የማያከብሩ ሹፌሮች ፖሊስ በሌለባቸው አካባቢዎች በግድ የለሽነት ስለሚነዱ ብዙ አደጋዎች ይፈጠራሉ:: ፖሊሶችም በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸውና ጥፋት በሚያጠፉ ሹፌሮች ላይ አስተማሪ ቅጣት ስለማይጣልባቸው ለአደጋዎች መባባስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ዘ-ሐበሻ ታምናለች::

Posted By-Lemlem Kebede

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s