በጉጂ በሃራ ቃሎና አካባቢው በአላሙዲን እና በመንግስት ላይ ሰፊ ተቃውሞ እየተሰማ ነው – ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል
February 8, 2016 Leave a comment
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ተጠናክሮ በተለያዩ ከተሞች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው:: እንደ ምንጮች ዘገባ በተለይ ከሕወሓት መንግስት ጋር በመዛመድ የሃገሪቱን ንብረት እየዘረፉ ነው በሚል ተቃውሞ የሚደርስባቸው ሼህ መሐመድ አላሙዲን የሚመሩት ሜድሮክ ኢትዮጵያ የሕዝብ ንብረትን ወስዶ እየበዘበዘ ነው በሚል ተቃውሞ እየደረሰበት ነው::
ዛሬ በጉጂ ዞን በሀራ ቃሎ ከተማና በተለያዩ የዞኑ ከተሞች በአላሙዲ ንብረት በሆነው ሜድሮክ ኢትዮጵያ እና በመንግስት ላይ ከፍተና የሆነ ተቃውሞ ሲሰማ ነው የዋለው:: ለተቃውሞ አደባባይ የወጣው ሕዝብ ለአላሙዲ በአካባቢው የተሰጠው መሬት የሕዝብ ሃብት ከመሆኑንም በላይ በርካታ የአካባቢውን ተወላጆች እና ነዋሪዎች የበይ ተመልካች እንደሚያደርግ በተቃውሞው እየተገለጸ ነው::
ሼህ መሐመድ አላሙዲ በሃገሪቱ ላይ የያዙትን የመሬት ቅርምት እንዲሁም ከሕወሃት መንግስት ጋር በመተባበር በሕዝቡ ላይ እያደረሱት ነው በተባለው የሃገር ሃብት ዝርፊያን በመቃወም በኢትዮጵያ እርሳቸው የሚያስዳደሩትይን ፔፕሲ እንዲሁም ሾላ ወተት እንዳይጠጣ ቦይኮት እንደተጠራባቸው መዘገቡ አይዘነጋም::
አላሙዲ የሃገር ሃብት የሆኑትን በጉጂ ዞን ለሻኪሶ እና ለአዶላ ከተማ አቅራቢያ አካባቢ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን እንዲሁም ከዚሁ ከለገደቢ ወርቅ ማዕድን ማውጫ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሳካሮ የተባለ የወርቅ ማዕድን ማውጫዎችን ተቆጣጥረዋል:: በተጨማሪም በመተከል ቤኒሻንጉል ጉምዝም እንዲሁ የህዝብ ሃብት የሆነውን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተጣጥረዋል::
Posted By-Lemlem Kebede
![]() |
![]() |