ቴዲ አፍሮ እና አብይ ላቀው ለኮራ የሙዚቃ አዋርድ ታጭተዋል | የሁላችንንም ድምጽ ይፈልጋሉ – እንምረጥ

አድናቂዎቹ የፍቅር ንጉሥ እያሉ የሚያሞካሹት ድምፃዊው ቴዲ አፍሮ እና በ ቅርቡ እንደገና ‘የኔ ሐበሻ’ አዲስ ነጠላ ዜማዋን የለቀቀችው ድምፃዊት አብይ ላቀው ለታዋቂው የኮራ የሙዚቃ አዋርድ እጩ ሆነው ቀረቡ:: ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ለዚህ ክብር የበቁት ሃገራችን ኢትዮጵያን ወክለው በመሆኑ የሁላችንም ድምጽ አስፈላጊ ነው::

የሌሎች ሃገራት ሕዝቦች የራሳቸው አርቲስት እንዲመረጥ ቅስቀሳ ከማድረግም በላይ በመምረጥም ላይ ይገኛሉ:: ከጃንዋሪ 20, 2016 ጀምሮ ለሕዝብ ይፋ የሆነውና ሕዝቡም በመምረጥ ላይ የሚገኝበት ይኸው የኮራ አዋርድ ቴዲ አፍሮን በምርጥ ዝነኛ ድምጻዊ (LEGENDARY AWARD) የውድድር ካታጎሪ እንዲሁም አብይ ላቀውን በምርጥ የሴት የባህል ድምፃዊነት (Best Traditional Female Artist) ካታጎሪ አብይ ላቀው ታጭተዋል::

የኮራ አዋርድ ከ55 ቀናት በኋላ አሸናፊዎች የሚታወቁ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ለሁለቱ ድምጻውያን በጽሁፍ መልዕክት ድምፃቸውን መስጠት ይችላሉ::

+248984000 ስልክ ቁጥሩ ሲሆን ለአብይ ላቀው KORA 74 የሚለውን ቴክስት በማድረግ መምረጥ ይቻላል::
እንዲሁም ለቴዲ አፍሮ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር KORA 156 በማለት ቴክስት በማድረግ መምረጥ ይቻላል:: አስታውሱ ለሁለቱም ድምፃውያን ድምጽ መስጠት ይቻላል – የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ::

INTERNATIONAL VOTING, SMS YOUR ARTIST’S VOTING CODE TO +248984000

Teddy Afro: KORA 156

Abby Lakew: KORA 74

ለበለጠ መረጃ እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ ለማወቅ
http://www.koraawards.com/en/news/how-to-vote-for-your-favourite-artists/#prettyPhoto

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s