መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ – በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል

girma wendimu

 

በተለያዩ ክሶች ተከሰው ላለፉት 76 ቀናት በ እስር ላይ የነበሩት ታዋቂው አጥማቂና መምህር ግርማ ወንድሙ ከእስር መፈታታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::

መምህር ግርማ በማታለል ወንጀል; ካለፈቃድ የቤተክርስቲያንን ስም ተጠቅመው አጥምቀዋል እንዲሁም ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ክሶች ተመስርተውባቸው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ መቆየታቸውን ጉዳዩን እየተከታተለች ስትዘግብ የነበረችው ዘ-ሐበሻ ማስታወቋ ይታወሳል::

መምህር ግርማ በተከሰሱበት ክሶች ሁሉ በተደጋጋሚ በዋስ ሲለቀቁ እንደገና ፖሊስ አዳዲስ ክሶችን እያመጣ እስከዛሬዋ ድረስ መቆየታቸው ይታወሳል::

ዛሬ ጃንዋሪ 13, 2015 (ጥር 4) በዋለው ችሎት መል አከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ፖሊስ ለአራተኛ ጊዜ አቅርቦት ከነበረው አንደኛ በጸበል አፍነው ሰው ገድለዋል በሚለው ክስ ፍርድ ቤቱ በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፈቅዷል::

መምህር ግርማ በ800 ሺህ ብር የማጭበርበር ክስ – በ40 ሺህ ብር ዋስ ተለቀው ነበር:: እንዲሁም በቤተክህነት ክስ 50 ሺህ ብር; እንዲሁም አዲስ በተከሰሱበት ክስ 50 ሺህ ብር ዋስ ያስያዙ ሲሆን በ76 ቀናት እስር ቆይታቸው መምህሩ ለዋስ 240 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በድምሩ አውጥተዋል::

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s