ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘውና በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው ከባድ ተቃውሞ እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ሰዓት በአጋዚ ጦር ዛሬ ብቻ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ 5 ማደጉ ተገለጸ::

oromo

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ከተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየመጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በፌደራልና አጋዚ ጦር በኢናንጎ ከተማ 3; በባኮ ከተማ 1 እንዲሁም በባቢቺ ከተማ 1  ወጣት (የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያድግ ይችላል) ተገድለዋል::

በአምቦ ሆስፒታል በቁስለኞች ተጥለቅልቋል:: በአጋዚ ጦር ተጎድተው በአምቦ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ከሚገኙት መካከል 1ኛ ታመን ውቤ ደምሰው 2ኛ ዓለሙ ለማ 3ኛ. ፍጹም አየለ 4ኛ. ሽመልስ ዘሪሁን 5ኛ ማሙሽ ሃያሉ 6ኛ ገመቹ ሃሬርሳ 7ኛ ሚሚ ቶሎሳ እንደሚገኙበት ታውቋል:: እንደዚሁም በጅማ ሆስፒታል ቁሰለኞችን ሲያክሙ የቆዩ የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀሩ ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል:: በሌላ ዜና የአዲስ አበባ እና የጂማ መንገድ መዘጋቱን የሚገልጹት ዘገባዎች በዲላ ከተማም እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ ነው ብለዋል:: በተቃውሞው የተነሳ መንገዱ በመዘጋቱ መኪኖች በጠቅላላ ቱሉቦሎ ላይ ቆመዋል:: በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ለማብረድ የፌደራል ፖሊስ እና የአጋዚ ጦር በየአካባቢው ያሉ የነዋሪዎችን ጭነት መኪናዎች አስገድደው በመውሰድ ሰራዊት በመጫን ሕዝብ ለመጉዳት እየተጠቁመበት እንደምገኙ የአይን እማኞች ይናገራሉ:: ዘ-ሐበሻ በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ እየተከታተለች መዘገቧን ትቀጥላለች::

Source-http://www.zehabesha.com

Posted By-Lemlemkebede

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s