አሰቃቂ አደጋ ኮልፌ ልኳንዳ አካባቢ ተከሰተ – ሚኒባስ ሙሉ ህፃናት ሕይወታቸው ማለፉ እየተነገረ ነው

Selman Siraj's photo.Selman Siraj's photo.
Selman Siraj's photo.Selman Siraj's photo.

በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ አስከፊነቱና አሳዛኝነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መጥቷል:: የዚህ ዜና ዘጋቢ የዘ-ሐበሻ ከፍተኛ ሪፖርተር በአንድ ወር ውስጥ 2 ጓደኞቹን ሕይወት በመኪና አደጋ አጥቷል:: ይህ የሚያሳየው ምን ያህል የመኪና አደጋ የሃገሪቱ ከፍተኛ ገዳይ ችግር መሆኑን ነው::

ዛሬ ከአዲስ አበባ ኮልፌ አካባቢ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሰረት የተፈጠረው አደጋ የህፃናትን ነብስ የቀጠፈ ሆኗል:: ፖሊስ ትክክለኛውን መረጃ አይስጥ እንጂ የዓይን እማኞች እንደሚገልጹት የሞቱት አንድ ሚኒባስ ሙሉ ህፃናት ናቸው::

ዛሬ ኮልፌ ልኳንዳ አቃቂ ድልድይ አካባቢ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ የነበሩ ህጻናት ላይ አንድ አይሱዚ መኪና የሚሄዱበትን ሚኒባስ ታክሲ በመግጨቱ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ በሚኒባሱ ውስጥ የሚጓዙት ህፃናትን ነብስ እንደቀጠፈ የአይን እማኞች ተናግረዋል::

ፖሊስ የሟቾችን ቁጥር ይፋ እንደሚያደርግ ሲገለጽ በምርመራ ላይ እንዳለም ታውቋል:: የአደጋውን ፎቶዎች ይመልከቱ::

ኮልፌና አካባቢዋ በለቅሶ ላይ ስትሆን አካባቢው ያለው ሕዝብ በከፍተኛ ሃዘን ላይ ይገኛል::

በዚህ አደጋ ስለ ቆሰሉት እና ስለሞቱት ወገኖች ተጨማሪ መረጃዎችን አጣርተን ይዘን እንመለሳለን::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s