ከሕወሐት መከላከያ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እየከዳ መሆኑ ታወቀ

clash

የህወሓት አባላት በሆኑ የይስሙላህ የጦር መኮንኖች ከታች እስከላይ ተጠርንፎ በጉልበት ተይዞ በአገር መከላከያ ስም እየተጠራ ነገር ግን በፀረ-ህዝብነት ሳይወድ በግድ እንዲሰለፍ እየተደረገ የሚገኘው ሰራዊት ስርዓቱን መክዳቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ፈፅሞ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡ በተለይም ደግሞ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት የከዳባቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡ በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ የሰራዊቱ አባላት ስርዓቱን ጥሎ መክዳት ተባብሶ የቀጠለ በመሆኑ የሰራዊቱ አባላት የትምህርት ማስረጃቸውንና ሌሎችን ሰነዶች ለመያዣነት እየተነጠቁ ይገኛሉ፡፡

በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ በሰፊው እየተተገበረ የሚገኘው ይህ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎችም የግል ሰነዶች ንጥቂያ በተለይም የሙያተኛ መኮንኖችን መክዳት ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ በሰራዊቱ ውስጥ እልህና ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል፡፡ ከጫፍ የደረሰ ኩርፊያም ጭምር አስከትሏል፡፡
በማዕከላዊ ዕዝ ዕና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ ሲከዱ ተይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሰራዊቱ አባላት እንዳሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ባልተጠበቀ ሰዓት ጥቃት ሊከፍቱ ይችላሉ ተብሎ በመስጋቱ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ታዞ በአካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ አየተደረገ ይገኛል፡፡

ምንጭ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s