ኢሕአዴግ ከዘር ፖለቲካ መዉጣት እንዳለበት ነበር የመከሩት ፖል ሄንዚ – ግርማ ካሳ

የአቶ መለስ ወዳጅ እና ልዩ አማካሪ የነበሩ፣ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ለኢሕአዴግ ተሟጋችና «ጠበቃ» ተብለው ይቆጠሩ ከነበሩ ጥቂት ግለሰቦች መካከል በቀዳሚነትና በዋናነት የሚጠቀሱ አሜሪካዊዉ ፖል ሄንዚ ነበሩ። እኝህ ሰው በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት በኢትዮጵያ የተፈጠረዉን ሁኔታ ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ አቶ መለስ በሕይወት የነበሩ ጊዜ ኢሕአዴግን የመከሩት አንዳንድ ምክሮች ነበሩ።

Girma kassa

ከ1991 በሁዋላ የተፈጠረዉ የፖለቲካ ስርዓት ብዙ ያልተጠና (Ad Hoc) እና ደርግ ሲወድቅ የነበረዉን ሁኔታ ያንጸባረቀ ነበር። ነገር ግን የማይቀየርና የማይሻሻል ተደርጎ ሊወሰድ አይገባዉም። ለምን ብዙ ጠቃሚ ያልሆኑ ሁኔታዎች እንዲከሰቱ አድርጓል» በማለት ነበር ፓል ሄንዝ የጻፉት። ጠቃሚና አላስፈላጊ ካሉዋቸው ነጥቦች መካከል፣ በኢሕአዴግ ስርአት ከመጠን ያለፈ ጊዜና ጉልበት ለብሄር ብሄረሰቦች በደልና ብሶት መሰጠቱ እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዉ ከልክ ባለፈ መልኩ በብሄር ብሄረሰብ ወይንም በዘር ላይ መሆኑ ይገኙበታል። በዚህም ምክንያት ፖል ሄንዝ ፣ ኢሕአዴግ በዘር ላይ ከማተኮር በአንድነት ላይ ማተኮር እንዳለበት፣ በዘር ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች ግንባር መሆኑ ቀርቶ፣ የኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ጥቅም ለማስጠበቅ የቆመ አንድ ሕብረ ሄራዊ ፓርቲ ቢሆን መልካም ሊሆን እንደሚችል ነበር የገለጹት። “If a majority of EPRDF leadership agrees that the entire party structure of Ethiopia should be changed, they would be well advised to pre-empt Kinijit by announcing the transformation of EPRDF into a party with a new name and new character. Among names that could be considered most appropriate might simply be “Ethiopian Democratic Party (EDP)” which would declare adherence to a platform for protecting the unity and integrity of the country, furthering its development and modernization in all respects with a firm commitment to democracy. ” ነበር ያሉት እኝህ ምሁር። በፕል ሄንዝ አስተያየት ላይ የራሳቸዉን ተጨማሪ አስተያየት የሰጡት በዉጭ አገር የሚኖሩ ፣ አፍቃሪ ኢሕአዴግ የሆኑት አቶ ሳሙዔል ገብሩ ሲጽፉ «The notion of placing one’s ethnic affiliation above one’s status as being an Ethiopian has plagued the country’s political development. Ethiopians tend to declare each other as either “the oppressed” or “the oppressor” without recognizing that at one point in our history we were all oppressed and oppressors » በማለት የአቶ ፖል ሄንዚ አስተያየቶች ይጋራሉ። ኢሕአዴግ፣ ከአራት በዘር ላይ የተደራጁ ድርጅቶች ስብሰብ መሆኑ ከበፊትም እንደማይዋጥላቸው የገለጹት አቶ ሳሙኤል «I would rather have the EPRDF as a political party and that be it. Too much concentration on one’s ethnicity further divides Ethiopia’s unity» ሲሉ ኢሕአዴግ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዉም ነበር:: እንግዲህ ኢሕአዴግ በምርጫ ዘጠና ሰባት የተመለከተዉን የሕዝቡን ስሜት አስተዉሎ፣ ኢትዮጵያዉያን የተዋለዱ፣ የተደባለቁ፣ ለመቶ አመታት ተከባብረዉ ተዋደዉ የኖሩ መሆናቸዉን ተረድቶ፣ እንዲሁም እንደ ፖል ሄንዝና እና አቶ ሳሙኤል ገብሩ ያሉ ያቀረቡትን አስተያየቶች ከግምት በማስገባት፣ ደረጃ በጠበቀ መልኩ ኢትዮጵያዉያንን በሚያስተሳሰርና በሚያቀራረብ አጀንዳዎች ዙርያ መስራት ብዙ ይጠበቅበታል። አቶ መለስ በሕይወት እያሉ ሕወሃት፣ ኦህዴድ፣ የአማራዉና የደቡብ ድርጅቶች በመዋሃድ አንድ አህዳዊ ፓርቲ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንዳንድ መረጃዎች ደርሰዉኝ ነበር። ይሄ ሂደት ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ የሞተ እስኪመስል ድረስ ዘረኝነቱ ተባብሷል። እንኳን እነዚህ ደርጅቶች አንድ ፓርቲ ሊሆኑ ቀርቶ ጭራሹኑ በመካከላቸውም የዘር ግጭቶች እየተፈጠሩ እንደሆነ ነው የምንሰማው።፡ የአኖሌና የጨለንቆ የጥላቻ ሃዉልቶች እየተናናሰ ለመጣው ዘረኝነትና የጥላቻ ፖለቲካ ሌላው ማሳያ ናቸው። አሁን ኢሕአዴግ በዘር ፖለቲካው ረገድ መፍትሄ ማምጣት ይቻል ዘንድ ከግንባርነት ወደ ዉህደት ቢሸጋገር ደርጅቱን የበለጠ ሊጠቅመው ይችላል ባይ ነኝ። ሆኖም ከአራት ድርጅቶች ግንባርነት ወደ አንድ ፓርቲ መዞር በራሱ መሰረታዊ ለውጥ ሊሆን አይችልም። መሰረታዊ ለዉጥ ማለት እነ ፓል ሄንዚ እንደመከሩት ኢሕአዴግ የአገሪቷን በዘር ላይ ያተኮረ ሕገ መንግስት እንዲሻሻል በማድረግ ዙሩያ ቀዳሚ በመሆን እንቅስቃሴዎች ሲጀምር ነዉ።

Source-zehabhesha.com

Posted  By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s