የሕወሓት ሰዎች ዶላርን በሰሜን አሜሪካ በ23 ብር እየመነዘሩ ሃብታቸውን በማሸሽ ላይ መሆናቸው ታወቀ

ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት ባለስልጣናት ከሃገር ቤት ሃብታቸውን ለማሸሽ እየጠቀሙበት ያለው ዘዴ የኢትዮጵያን ባንኮች ከመጉዳቱም በላይ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስፈሪ ዳመና እንደጣለበት ተሰማ:: በአሁኑ ወቅት የሕወሓትና የተላላኪዎቹ ድርጅቶች ባለስልጣናት በሙስና ያከበቱትን ሃብት እያሸሹ ያሉት እዚህ ሰሜን አሜሪካ ወደ ሃገራቸው ዶላር መላክ የሚፈልጉትን በ23 ብር ሃገር ቤት ላይ እንመነዝርላችኋለን በሚል እንደሚቀበሉና በዚህም ጥቁር ገበያ የሕዝብ ሃብት እየሸሸ መሆኑ ተጋልጧል:: በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ዲሲ; በሲያትል; በዴንቨር; በሚኒያፖሊስ; በአትላንታ; በዳላስ; በቺካጎ; በሂውስተን; በኦሃዮ; በፖርትላንድ; በላስቬጋስ; በካሊፎርኒያ የተለያዩ ከተሞች; በአሪዞና በተዘረጉ ኔትወርኮች ዶላር በጥቁር ገበያ 23 ብር እየተመነዘረ መሆኑ ታውቋል:: የገንዘቡ ዝውውር የሚደረገው ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች ባሉ ኔትዎርኮች መካከል ዶላሩን እዚሁ ይሰጡና ሃገር ቤት በግለሰቦች አማካኝነት በ23 ብር ምንዛሬ ይሰጣል:: ዘ-ሐበሻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድረገጽ ባገኘችው መረጃ መሰረት በዛሬው ዕለት የዶላር ምንዛሬ ዋጋ 20.85 ሲሆን በ23 ብር በጥቁር ገበያ እየሸጠ ይገኛል:: ዶላር በሕገወጥ መንገድ እንዲህ መተላለፉ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መንግስት ዘንድ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት የሚያባብሰው መሆኑ እየታወቀ የሕወሓት ሰዎች እንዴት እንዲህ ባለው ሕገወጥ ተግባር ላይ እንደተሰማሩ የሚያስገርም ነው የሚል አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች ከጥቂት ጊዜያት በፊት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “የኢትዮጵያን መንግስት በኢኮኖሚ ማዳከም ካስፈለገ ከውጭ የሚላኩ ዶላሮች በኢትዮጵያ ባንኮች በኩል መተላለፍ የለባቸውም:: ሕዝቡ ዶላሩ መንግስት እጅ በማይገባበት መልኩ ገንዘቡን ይላክ” ማለታቸውን ይጠቅሳሉ::

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s