በሊብያ ያተኮረ የዓለም አቀፍ ሚኒስተሮች ስብሰባ

የአኅጉራዊና የሰሜን አፍሪቃን አከባቢ ጸጥታ ለማረጋገጥ በሊብያ ሰላም መስፈን እንዳለበት ከፍተኛ የዓለም አቀፍ መሪዎች ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ

የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን በሊብያ ላይ አተኩረው ከሚኒስተሮችና ከከፍተኛ የዓለም አቀፍ መሪዎች ጋር በሊብያ ሰላምና ጸጥታ ላይ በማተኮር ዛሬ በሚጠናቀቀው የተ.ደ.መ. ጠቅላላ ሰባኛ ጉባኤ ላይ የጎን ስብሰባ አካሄደዋል።

ይህ በትናንትናው አርብ እለት፣ በአውሮፓ አቆጣጠር መስከረም 2008 ዓ.ም በኒው ዮርክ ከተማ የተካሄደው ውይይት ሰላም በሊብያ እንዲሰፍን ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን ለዓለም መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

ስብሰባው በአኅጉራዊና በሰሜን አፍሪቃ አከባቢ ጸጥታና ሰላም ለማስፈን ያለመ ሲሆን፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የአፍሪቃ ሕብረትና የአውሮፓ ሕብረት የሊብያ ግብጽ ሱዳን ናይጄርያና ሌሎች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ወካዮችን አሳትፋል።

በአሁኑ ጊዜ በሊብያና በአከባቢዋ ባለው ቀውስ በብቸኛ አገር መሪነት ወይም በጦር ሃይል መፈታት እንደማይገባው ተሳታፊዎቹ ተቃውሞዎቻቸውን ገልጸዋል።

በማስቀጠል፣ ዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ በሊብያ ፖለቲካዊ መስመር ለማስፈን የሚችለው ሕግና ሰብዓዊ መብቶች መጀመርያ መከበር እንዳለበት የዓለም አቀፍ መሪዎች ተስማምተዋል።

በዚ አጋጣሚ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ “የሊብያን መሪዎች፣ በተለይ ዛሬ ከኛ ጋር ተሰብስበው የሚገኙት ወኪሎች፣ የሊብያ ሕዝብን ስቃይና መከራ ለማቆም ባንድ መንፈስ መስማማት አለባቸው” ብለዋል።

Source-voa.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s