ኒው ዮርክ፣ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ መከፈት

Image result for Pan ki mun

የተመድ ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን አውሮጳ ስደተኞችን በመቀበሉ ረገድ ብዙ ድጋፍ እንድታደርግ ጠየቁ። ዋና ጸሐፊው ከ160 የሚበልጡ አባል ሃገራት የተገኙበትን  70 ዓመት የሆነውን የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በከፈቱበት ወቅት ባሰሙት ንግግራቸው፣ አውሮጳ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የዓለምን ርዳታ መጠየቋን አስታውሰዋል። የተመድ ርዳታ ሰጪ መስሪያ ቤቶች በጀት በወቅቱ እጅግ ንዑስ መሆኑን የገለጹት ፓን በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 60 ሚልዮን ሰው በስደት ላይ እንደሚገኝ እና ሌሎች 100 ሚልዮንም ሰብዓዊ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው  አስታውቀዋል።  ብዙዎቹ ስደተኞች የርስበርስ ጦርነት የሚካሄድባት የሶርያ ዜጎች መሆናቸውን ያስታወቁት የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ፓን ኪ ሙን ለዚችው ሃገር ውዝግብ መፍትሔ ለማስገኘት አምስት ሃገራት፣ ዩኤስ አሜሪካ፣ ሩስያ፣ ሳውዲ ዐረቢያ፣ ኢራን እና ቱርክ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ አስረድተዋል።

Source-dw.de.com

Posted By-Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s