የደቡብ ሱዳን መንግሥት ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር እሁድ ኢትዮጵያ የገቡት ተገደው እና ጫና ተደርጎባቸው እንደሆነ ገለጹ

Fahnen der IGAD-Mitgliedsländer

የደቡብ ሱዳን መንግሥት አዲስ አበባ ውስጥ ከተቃዋሚዎች ጋር ለሚኪያሄደው ድርድር ፕሬዚዳንቱን ወደ ኢትዮጵያ መላኩ ተዘገበ። ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር እሁድ ኢትዮጵያ የገቡት ተገደው እና ጫና ተደርጎባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር አዲስ አበባ እንደማይሄዱ፤ ተደራዳሪዎቹም ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተዘግቦ ነበር። ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር በድርድሩ እንደማይገኙ፤ ይልቁንስ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄምስ ዋኒ ኢጋ ለድርድር ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ አቴኒ ዌክ ቅዳሜ ዕለት ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረው ነበር።

ቅዳሜ ዕለት ዘግየት ብሎ በወጣ ዜና ደግሞ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ድርድሩን አቋርጧል መባሉን አስተባብሏል። እንደውም መንግሥትን የሚወክሉ ተደራዳሪዎች እዛው አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛሉ ብሏል። በጥቂት ሰአት ልዩነት የሚወጡ መረጃዎች እጅግ የተጣረሱ መኾናቸው እየታየ ነው።

አደራዳሪዎች ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር ከተቀናቃኛቸው የአማፂያን መሪ ሪይክ ማቻር ጋር ተገናኝተው የስምምነት ፊርማ እንዲያኖሩ ይሻሉ። የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና አማፂያን የሠላም ድርድር አድርገው ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ ዓለም አቀፍ ጫናው አይሎባቸዋል።

ሱዳን ትሪቡን የሠላም ድርድሩ ተሰናክሏል ሲል ዘግቦ ነበር። ዐርብ እለት አዲስ አበባ መግባት ይጠበቅባቸው የነበሩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ተደራዳሪዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማዘዛቸውን ጋዜጣው አክሎ መዘገቡን የጀርመን ዜና አገልግሎት አትቷል። ከኹለት ቀናት በፊት ደግሞ የደቡብ ሱዳን አማፂያን ጄነራሎች ከመሪያቸው ሪይክ ማቻር ጋር ባለመስማማት ተገንጥለው መውጣታቸውም ተጠቅሷል።

ሰኞ በሚጠናቀቀው ቀነ-ገደብ ኹለቱ ተቀናቃኝ ወገናት ከአንዳች ስምምነት ላይ የማይደርሱ ከኾነ በአመራሩ ላይ «ብርቱ ጣጣ» ሊከተል እንደሚችል ዲፕሎማቶች አስጠንቅቀዋል።

እጅግ ዘግናኝ ድርጊቶች በተስፋፉበት የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና የአማፂያን ግጭት የተነሳ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ተገድለዋል። ሚሊዮኖች ለስደት ተዳርገዋል። ጦርነቱ የተለየ ጎሳን በጅምላ የመጨፍጨፍ እና አስገድዶ የመድፈር ገፅታ እየታየበት ነው ተብሏል። የደቡብ ሱዳን ግጭት ሰዎችን ከነሕይወት ማቃጠል፣ መስለብ እና ህፃናትን እርስ በርስ አሥሮ ጎሮሮዋቸውን በስለት መቁረጥ ደረጃ መድረሱ ተገልጧል። የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት 20 ወራትን አስቆጥሯል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ

Source/dw.de.com

Posted By/Lemlem Kebede

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s